አንድ መሆን ማለት እርስ በርስ መደሰት ነው

አንድ መሆን ማለት እርስ በርስ መደሰት ነው

እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። – 1 ጴጥ 3፡1-2

አንዳችሁ በአንዳችሁ መደሰት ስትጀምሩ በጋብቻችሁ ዉስጥ ታላቅ ደስታ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያደረጋችሁ እንድትመሰቃቀሉ እንዳልሆነ ታዉቃላችሁ? እርስ በእርስ እንድትፋለሙ አላጣመራችሁም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ሚስት በባሏ እንድትደሰት ይናገራል ይህ ለሁለቱም እንደሚሰራ አምናለሁኝ፡፡ ሆኖም ግን “ታዉቂያለሽ? በባሌ ደስተኛ ነኝ”፣ “በሚስቴ ደስተኛ ነኝ” የሚል ሰው የምሰማዉ አልፎ አልፎ ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን በጋብቻ ውስጥ እርስ በእርሳችን እንድንደሰት ይፈልጋል፡፡ እርሱ አንተና አጋርህ እንድትስቁና እንድትደሰቱ ይፈልጋል፡፡ ይኼ ሁሌ እንደማይሰራ አዉቃለሁ፤ ጋብቻ ብዙ ተግዳሮቶች አሉትና፤ ነገር ግን ከልዩነቶቻችሁ በሻገር እግዚአብሔር ስለ አጋራችሁ አስደናቂ ነገር እንዲያሳያችሁ ጠይቁ፡፡ እግዚአብሔር አጋራችሁን የሰራበትን መንገድ ጠይቁ እርሱ ይወዳቸዋል ልክ ለአንተ እንዳደረገዉም ለእነርሱም ሞቶአልና።

አንዳችሁ ለአንዳችሁ ያላችሁ እይታ እንደ እግዚአብሔር ሲሆን በተፈጥሮ ልባችሁን ደስታ ይሞላል ከዚያም በአጋራችሁ ለመደሰት ትችላላችሁ።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በባለቤቴ መደሰት እፈልጋለሁ፤ ጋብቻ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ እንኳ ደስታን መፈለግና መደሰት አንተ የሰራህባቸዉን መንገድ ማየት እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon