አንድ ሰው እየጸለየልህ ነው።

አንድ ሰው እየጸለየልህ ነው።

ስለ እነሱ እየጸለይኩ ነው። (ዮሐንስ 17:9)

ኢየሱስ እንደሚጸልይልን እናውቃለን። በሉቃስ 22፡32 ላይ ለጴጥሮስ “በተለይ ስለ አንተ ጸለይኩ” አለው። በዛሬው ክፍል ስለ ደቀመዛሙርቱ “እኔ ለእነርሱ እየጸለይኩ ነው” ይላል። ደግሞም በዮሐንስ 17 ውስጥ፣ በመቀጠል “ስለእነዚህ ብቻ አልጸለይም፤ ነገር ግን በእኔ ሊያምኑ ላሉት ጭምር ነው” ያ ማለት ደግሞ አንተ እና እኔ ማለት ነው (ቁ. 20)።

አማላጅ ምንድን ነው የሚያደርገው? አማላጅ በእግዚአብሔር እና በግለሰብ መካከል ባለው ክፍተት ቆሞ ስለ ሌሎች ይጸልያል። ሁላችንም በእግዚአብሔር እና በእኛ መካከል ክፍተት አለብን። በሌላ አገላለጽ፣ እኛ የእርሱን ያህል ቅዱስ አይደለንም፤ ነገር ግን ኢየሱስ እዚያ ክፍተት መካከል በመቆም እግዚአብሔርን እና እኔን – ወይም እግዚአብሔርን እና አንተን አንድ ላይ በማምጣት ከእርሱ ጋር ህብረት እንዲኖረን እና እርሱ ለጸሎታችን ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል። ልባችን ትክክል እስከ ሆነ እና በኢየሱስ እስካመንን ድረስ የምናደርጋቸውን ፍጽምና የጎደላቸው ነገሮች ሁሉ ጣልቃ እንደሚገባ፣ እንደሚያስተካክል ደግሞም ኃላፊነት እንደሚወስድ ማወቁ አያስደንቅም? ኢየሱስ ስለአንተ ሲጸልይ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆሞ በዓይነ ሕሊናህ እንድታይ እፈልጋለሁ። ይህንን ስታደርግ ፍጹም ስላለመሆንህ በሚያቀርበው ምልጃ አማካይነት ኃላፊነት እንደሚወስድ ማመን ትችላለህ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ኢየሱስ ስላንተ እየጸለየ ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon