የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጠ፡፡ ሮሜ 12 2
እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ የተቀበልኩት በዘጠኝ ዓመቴ ነበር፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኃጥያተኛነቴ ገብቶኝ ለምህረት መፀለይ ጀመርኩ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ተወልጃለሁ፡፡ ነገር ግን በሕይወቴ ምን እንደተከናወነ በእርግጥ አልተረዳውም ነበር፡፡ ምንም ትምህርት በጉዳዩ ስላላገኘው ምንም እንኳ ብርሃን በውስጤ ቢኖርም በጨለማ ውስጥ ነበርኩ፡፡
እንደ አንድ ወጣት ቤተክርስቲያን በሙሉ እምነት እሄድ ነበር፣ ተጠመቁ፣ የእምነት ማዳኛ ትምህቶችን ወሰድ፣ ማንኛውንም ነገር ሌሎች የሚያደርጉትን አደረኩ፡፡ እስከዚህ ድረስ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር በመቀራረብና በወዳጅነት ውስጥ ያለውን ደስታ አላጣጣምኩትም፡፡ ብዙ ሰዎች ዛሬም ሆነ ባለፉት ሺህ ዓመታት በዚህ ሁኔታና ደረጃ እንደሆኑና እንደለፉት አምናለሁ፡፡
ምንም እንኳ እኔ ጥሩ ኃይማኖተኛ ለመሆን የበኩሉን ጥረት ባደርግም ኢየሱስ ግን ለእኛ ኃይማኖትን ሊሰጠን አልሞተም፡፡ እርሱ የሞተው የግል የሆነ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር በእርሱና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል በእኛ ውስጥ እንዲኖር ባደረገው በእርሱ በኩል ነው፡፡
ከላይ እንደገለፅኩት እኔ ከመንፈስ ተወልጄ ነበር፡፡ ነገር ግን በእርግጥ ምን ማለት እንደሆነ መገለጥ አጥቼ ነበር፡፡ ሰዎች በጣም ባለፀጎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በእምነት እነርሱ ድሆች ናቸው፡፡ ሕይወታቸውም በችጋር ከሚኖሩ ሰዎች ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ሰዎች ትልቅ ውርስ ቢኖራቸውና ነገር ግን የማያውቁ ከሆነ ሊጠቀሙበት አይችሉም፡፡ የዛሬው ጥቅስ እግዚአብሔር ለእኛ ዓላማና መልካም ሃሣብ እንዳለው ይህንን በጎና መልካም የሆነውን ለማወቅ ደግሞ በአእምሮ መታደስ ይፈልጋል፡፡ (ሮሜ 12 1-2 ተመልከት) እኛ አእምሮአችንን ስናድስ መልካም ባሕሪና ጥሩ የሆነ ሃሣብ እንደሚኖረን ከእግዚአብሔር ቃል እናገኛለን፡፡ እንደእግዚአብሔር ሃሣብ ለማሰብ እንዴት እንደምናስብ መማር አለብን፡፡
ዛሬ የእግዚብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር የሚያስበውን አስብ፡፡