እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው፡፡ – ኤፌ 4፡24
በኋላ ታሪካችሁ ውስጥ ያጋጠሟችሁ አሳማሚ ነገሮች መጥተው ሄደዋል፡፡እግዚአብሔር የህይወታችሁን እያንዳንዱን ቀን እንድትደሰቱበት አሁንም ይፈልጋል፡፡ የኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የገዛላችሁን የተትረፈረፈ ህይወት ለመያዝ አዕምሯችሁን እስክታሳምኑት ድረስ ይህ ነገር መሆን አይችልም፡፡ እስከዚያ ዲያብሎስ ሊወስድባችሁ ይሞክራል፡፡
ኢየሱስ ሲናገር ሌባው የሚመጣው ለመስረቅ ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ነው፡፡ እኔ ግን ህይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣሁ ዮሀ.10፡10፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው እና ስለእኛ የሞተው የተትረፈረፈ ህይወት እንዲኖረን ነው!
እርሱ በሚሰጠው ህይወት አዲስ ፍጥረት ሆናችኋል፡፡ የድሮ ነገሮች በክርስቶስ ያገኛችሁትን አዲሱን ህይወታችሁን እንዲያውኩት መፍቀድ የለባችሁም፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ እንዳለ አዲስ ፍጥረት በእግዚአብሔር ቃል አዕምሯችሁን ልታድሱ እና ስሜቶቻችሁ ሊፈወሱ እና ሊታደሱ ይችላሉ፡፡ ኢየሱስ በገዛላችሁ አዲስ ተፈጥሮ ስትኖሩ የእግዚአብሔር መልካም እቅዶች መከፈት ይጀምራሉ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚብሔር ሆይ በየዕለቱ በንቃት ኢየሱስ የገዛልኝን አዲሱን ተፈጥሮ መልበስን እመርጣለሁ፡፡ በክርስቶስ እንዳዲስ ደስተኛ ፣ ሰላማዊ እና ሙሉ ፍጥረት ሆኜ ተፈጥሬያለሁ፡፡