ደግሞም በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ – ኤፌ 4፡23
መጽሀፍ ቅዱስ በበርካታ አዳዲስ ጅማሬዎችን በተለማመዱ ሰዎች ታሪክ የተሞላ ነው፡፡ ሙሴ ለአርባ ዐመታት በእረኝነት ከቆየ በኋላ ነበር መሪ ለመሆን የበቃው፡፡ እግዚአብሔር ሕይወቱን ቀይሮ ታላቅ ሐዋሪያ ሆኖ ከመለወጡ አስቀድሞ ጳውሉስ ክርስቶስን አጥብቆ የሚጠላ ሰው ነበር፡፡
ኢየሱስ እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ይህ ታላቁ የሕይወታችን አዲስ ጅማሬ ነው፡፡ አዲስ ፍጥረት በመሆን በሕይወት አዳዲስ የሕይወት ዘይቤ ለመከተል የጀመርንበት ቀን ነው፡፡ የዚህ አዲስ ሕይወት ልምምድ መጀመሪያው የቀረበልን አዲስ ሕይወት አምኖ መቀበል ነው፡፡
ኤፌሲዮን 4፡23 ቀጣይነት ባለው መልኩ አዕምሯችን እና አቋማችን መታደስ ይኖርበታል፡፡ ስለ ታላላቅ ሰዎች በቅዱስ ቃሉ ውስጥ በማንበብ ራሳችንን በንጽጽር በማየት እንደ እነርሱ መሆን የማንችል አድርገን እንቆጥራለን፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ዓይነት ሀሳብ የምናስብ ከሆነ በፍጥነት አዕምሯችንን ማደስ ይኖብናል፡፡
በስሜት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ለማሰብ መምረጥ አለብን፡፡ የእርሱን ፍቅር በመቀበል የአዳዲሰ ነገሮች ጅማሬዎችን ተለማመድ፡፡ ከውስጥ ወደ ውጭ በሆነ መለወጥ ጌታ በፍጹም ለውጦኛል የሚል አቋም በመያዝ የምትኖር ከሆነ ሕይወት በጣም ጣፋጭ ትሆንልሃለች፡፡ እግዚአብሔር አዳዲስ ጅማሬዎች ይሰጠኛል በመሆኑም ከፊቴ ትልልቅ ነገሮች ይጠብቁኛል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታ ሆይ አዕምሮዬን በቃልህ ማደስ እፈልጋለሁ፡፡ ለጳውሎስ እና ለሙሴ እንዳደረክላቸው ለእኔም አዲስ ጅማሬ እና ጥሪ እንዳለህ አውቃለሁ፡፡ ያረጀውን ሁሉ ዛሬ እንደምታሳልፈው አምኘ እቀበለዋለሁ፡፡