ኢየሱስን ተመልከት

‹‹የእምነታችንንም ራስና ፈፃሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ…. ›› ዕብ 12 1-2

ብዙ መልካም የሆኑ ነገሮች የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆናቸውን ለማወቅ የምንችልባቸው የእግዚአብሔር ቃል በግልፅ ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ነገሮች ወይም ጥያቄዎች ከእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ መልስ የማናገኛቸው አሉ፡፡ ስለአንድ ነገር በቀጥታ በቃሉ ላልተገለጠ ጉዳይ በቃሉ በዚህ ምዕራፍና በዚህ ቁጥር መሠረት ብሎ ማለት ለማልችለው እንዲህ በማለት እፀልያለሁ፡፡

‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህንን እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ከእራሴ ፈቃድ በላይ የአንተን ፈቃድ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ስለዚህ የእኔ ጥያቄ የአንተ ጊዜ ካልሆነ ወይም የጠየኩት ወይም የፀለይኩት አንተ ለእኔ ያላሰብኩት ከሆነ እባክህ ለእኔ አትስጠኝ አሜን፡፡››

አንዳንድ ጊዜ በስሜት ተገፋፍተን አንዳንድ ነገሮችን ከእግዚአብሔርና የእርሱ ፈቃድ መስሎን ልናደርግ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ነገሩን ከጀመርን በኋላ ምናልባት ነገሩ መልካም ሃሣብ ብንሆን ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ነገሩ ውጤታማ እንደማሆን ልንረዳው እንችላለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በእርሱ ሃሣብና ፈቃድ ያልመነጨውን ነገር ለማጠናቀቅ አይገደድም፡፡ ለጀመርነው ዕቅድ መፀለይ እንችላለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ጉዳዩን ሊፈጽምልን ካልፈለገ ዝም ብሎ ነገሩ መልካም ስለሆነ ብቻ እየተቀመጠ አይፈጽምም፡፡ ከእርሱ ያልመነጨውን ማንኛውንም ነገር ለመፈፀም አይገደድም፡፡ መልካም የሚመስሉ ነገሮችን ከመጀመራችን በፊት በጣም መጠንቀቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ መልካም ነገሮች እግዚአብሔር ለእኛ ላለው በጣም መልካም ነገሮች ጠላቶች ናቸውና፡፡ አንድ ሃሣብ ወደ አንተ ሲመጣ በቀጥታ ወደ ተግባር ከመግባትህ በፊት ጊዜ በመውሰድ የእግዚአብሔር ፈቃድና ሃሣብ ለመሆኑ መንፈስ ምስክርነትና የውስጥህን ሠላም አረጋግጥ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የአንተ ጥሩ ሃሣቦች የእግዚአብሔር ሃሣቦች እንደሆኑ እርግጠኛ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon