ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው

ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው

…እግዚአብሔር ፍቅር ነውና. – 1 ኛ ዮሐ 4፡8

ፍቅር ሊታይ የሚችል ነገር ነው፡፡በህይወታችን ውስጥ በሚሰራው የመንፈስ ፍሬ፣በባህሪያችን እና ሰዎችን በምንይዝበት መንገድ ይታያል፡፡ፍቅር ብዙ መገለጫ ወይም ልናየው የምንችልበት ብዙ መንገድ አለው፡፡ለምሳሌ የአልማዝ ቀለበት ብርሃን ላይ ሲሆን እንደምናዟዙርበት ሁኔታ በተለያየ አቅጣጫ ያንጸባርቃል፡፡እንደምናይበት ሁኔታ ፍቅርም በተለያየ መንገድ ያንጸባርቃል ብዬ አምናለሁ፡፡

1 ኛ ቆሮ.13፡4-7 ስለ ፍቅር ብዙ መገለጫ ምሳሌዎችን ይሰጠናል፤

  • ፍቅር ታጋሽ ነው-ረጅም ጊዜ ከአንድ ነገር ጋር የመቆየት ብቃት አለው፡፡
  • ፍቅር አይመቀኝም-የሌለውን አይፈልግም፡፡
  • ፍቅር አይመካም፣አይታበይም-ወደራሱ ትኩረትን አይስብም፡፡
  • ፍቅር ያልሆነ ነገር አያደርግም፡፡
  • ፍቅር ራስወዳድ አይደለም፡፡
  • ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፡፡
  • ፍቅር ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል!

እነዚህ ሌሎችን ልንወድ የሚገባባቸው በጣም ጥቂት መንገዶች ናቸው…እግዚአብሔርም እኛን የወደደባቸው መንገዶች ናቸው፡፡አንደኛ ዮሐንስ 4፡8 እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ይላል፡፡እግዚአብሔር ከሌሎች ጋር ፍቅሩን እንድንካፈል ወዶ አድኖናል፡፡

እግዚአብሔርን ለመምሰል ፍጹም ምሳሌው የሆነውን እና በ1ኛ. ቆሮንቶስ 13 ላይ ያለውን ዝርዝር ሁሉ የኖረውን ኢየሱስን መመልከት አለብን፡፡በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ሁልጊዜም ሰዎች እንኳ ሲቃወሙት የተመላለሰው በፍቅር ነበር፡፡

ቆላሲያስ 3፡12-14 የእግዚአብሔር ምርጦች እንደመሆናችሁ …በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት፡፡ይላል፡፡ልክ እንደ ኢየሱስ ራሳችንን በፍቅር እናልብስ እና ምሳሌውን መከተል መርጠን ለእግዚአብሔር ክብር እናምጣ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ እኔን በመውደድ ፍቅር ምን እንደሆነ አሳይተኸኛል፡፡የኢየሱስን ምሳሌ እንድከተል እና በዕለት ተዕለት ህይወቴ ሁሉንም የፍቅር መገለጫዎች እንድኖር እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon