የእግዚአብሔር መንፈስ፣የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኀይል መንፈስ፣የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። (ኢሳያስ 11፡2)
እግዚአብሔር በህይወታቸው የመገኘቱን ክብር የሚያሳዩ ሰዎችን ይፈልጋል። በሕይወታቸው ውስጥ በእያንዳንዱ ትንሽ ነገር እርሱን የሚታዘዙ ሰዎች ይሆናሉ። መታዘዝ ህሊናችንን ከመቆሸሽ ይጠብቅልናል ደግሞም ለእግዚአብሔር ክብር እንድንኖር ያደርገናል።
የዛሬው ክፍል ስለ ኢየሱስ ትንቢት መሆኑን እናውቃለን፣ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ በውስጣችን ካለ እና በእኛ የሚኖር ከሆነ በዚያን ጊዜ በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ እንደሰታለን። ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ምክር፣ ሀይል እና እውቀት ይኖረናል።
እነዚህ ጭዋነቶች ባሉበት ችግሮች ይፈታሉ። ለመንፈስ መሪነት የምንታዘዝ ከሆነ በውዥንብር ውስጥ መኖር የለብንም። ለእርሱ በአክብሮት የምንገዛ እና የምንታዘዝ ከሆንን ጌታ የጠነ ምክርን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን እና ሀይልን ይሰጠናል።
ማስተዋል እንዲኖራቸው የሚፈልጉ፣ ከእግዚአብሔር መስማት የሚፈልጉ፣ጥበብ እና እውቀት እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራት እና አክብሮት ሊኖራቸው ይገባል። አክብሮታዊ ፍርሃት ማለት እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ደግሞም እርሱ እውነት መሆኑን ማወቅ ነው። እርሱ ጓደኞቹ ብሎ ጠርቶናል፣ ወንዶች ልጆቹ እና ሴቶች ልጆቹ፣ ነገር ግን በአክብሮታዊ መታዘዝ እናከብረዋለን።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ማንኛውም ነገር ለራስህ ጥቅም ነው፤ ስለሆነም ዛሬ እና በየቀኑ ለመታዘዝ ፍጠን።