ኢየሱስ ፈሪሳዊ አይደለም

ኢየሱስ ፈሪሳዊ አይደለም

በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። – ዮሐ 3፡18

እግዚአብሔር ህዝቡን በመገፋት ከደረሰባቸዉ የቀደመ ጉዳት ሊፈዉሳቸዉ ይፈልጋል፡፡ እርሱ ፈጽሞ እንደማይተዉህ እንድታዉቅ ይፈልጋል፡፡ በማቴ 11፡28 እርሱ ያለዉ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ነዉ፡፡ ይህ የተባለዉ ፍጹም መሆን ፈልገዉ ለሚሞክሩና ሲወድቁ በጥፋተኝንት ስሜት ለሚጠቁ ሰዎች ነዉ፡፡

በዮሐ 3፡18 ኢየሱስ በፈርሳዊያን ህግ ሥር ለመኖር ለሚጣጣሩ ሰዎች ነዉ የተናገረዉ፡፡ ፈርሳዊያንን ለመድረስ ነዉ የተናገረዉ ዛሬም ፈርሳዊያን በዙሪያችን አሉ፡፡ “ይህንንና ያንን በጥንቃቄ ካደረግህ እወድሃለሁ ካልሆነ ደግሞ አስወግድሃለሁ” የሚሉአችሁ ሰዎች እንደሚኖሩ እርጠኛ ነኝ፡፡

ኢየሱስ ፈርሳዊ አይደለም፡፡ በዮሐ 3፡18 የሚለዉ በእርሱ የሚያምን ፈጽሞ እንደማያፍር ነዉ፡፡ በእርሱ እመን፣ እርሱን ውደድ፣ ጥራዉ፣ በእርሱ ታመን ተደገፍ፡፡ ከዚያም እርሱ ወደሚሰጥህ የተትረፈረፈ የደስታ ህይወት መቀላቀል ትችላለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ስለወደድከኝና ሁሌም ስለምትቀበለኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በአንተ አምናለሁ፣ እወድሃለሁ፣ እታመንሃለሁ፣ ባለኝ ሁሉ በአንተ እደገፋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon