እጅግ ከብዶኛልና ይህን ሁሉ ህዝብ ብቻዬን ልሸከም አልችልም፡፡ – ዘሁ 11፡14
በዘሁልቁ 11 ላይ በጭንቀት ውስጥ ስናልፍ ምን ልናደርግ እንደምንችል ሙሴ ምሳሌ ሰጥቶናል፡፡ እስራኤላዊያንን በምድረበዳ በሚመራ ወቅት ፤ አስራአንድ ቀን ብቻ መፍጀት የሚገባው ጉዞ አርባ አመት ሲወስድ ስለነበረው ጫና ያወራል!
ህዝቡ በድብርት ውስጥ እና ካሉበትሁኔታ የተነሳ በለቅሶ ውስጥ ነበሩ፡፡በቁጥር 14 ላይ ሙሴ እግዚአብሔርን “እጅግ ከብዶኛልና ይህን ሁሉ ህዝብ ብቻዬን ልሸከም አልችልም፡፡” ብሎ ይነግረዋል።
ልክ እንደሙሴ እኛም “ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል” ማለት እንችላለን፡፡አዎ መጽሀፍ ቅዱስ ፊሊጲሲዩስ 4፡13 ላይ ሲናገር ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ይላል፡፡ነገር ግን ይሄ የሚያመለክተው የተለያዩ ችግሮች እና ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እግዚአብሔር በዚያ ውስጥ እንደሚረዳን ነው፡፡
ልክ የአምስት ልጆ እናት ሆና ሙሉጊዜ የምትሰራ፣ በቤተክርስቲያን ቦርድ ውስጥ የምታገለግል እና ሌሎችም ኃላፊነቶች ያሉባት ሴት አይነት በጣም ብዙ ኃላፊነቶችን ተቀብለን ከጥቅም ውጪ መሆን አለብን ማለት አይደለም፡፡
አንዳንዴ በቃ ከአቅም በላይ ይሆናል… እናም ደግሞ ይሄንን ማመን ምንም ችግር የለውም፡፡እግዚአብሔር በወሰነው መሰረት በህይወት ለመደሰት አንዳንድ ነገሮችን “እምቢ” ማለትም ችግር የለውም፡፡
እዚህ ጋር አንድ ነገር ልበል፡እኔ እና እናንተ እንደሌላው ሰው መሆን የለብንም ወይም ሌላ ሰው ጋር መፎካከር የለብንም፡፡እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን ብዙ ስራ እንዲሸከሙ አድርጎ ነው የፈጠራቸው ብዙ ሰዎች ግን በዚያ መንገድ አይደለም የተፈጠሩት፡፡
እያንዳንዳችን እግዚአብሔር የፈጠረንን ነው መሆን ያለብን፤ያንን ስለሆንን ደግሞ ይቅርታ መጠየቅ የለብንም፡፡እኛ እያንዳንዳችን በጭንቀት እና በጫና ራሳችንን ከማሳመም ይልቅ ህይወታችንን ተደስተን እንድንኖርበት እግዚአብሔር የመደበልንን ሚዛናዊ የሆነ ኃላፊነታችንን ማግኘት ይኖርብናል፡፡
ከአቅማችሁ በላይ ሲሆን እንደ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ሂዱ፡፡የተረጋጋ እና ጤናማ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖራችሁ ይረዳችኋል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ፣አንዳንድ ጊዜ መረጋገት እና ተጨማሪ ኀላፊነትን ላለመቀበል “እምቢ” ማለት ይከብደኛል፡፡በአንተ ሰላም ውስጥ እንድኖር እና ህይወትን እንዳጣጥመው ለእኔ ከፈጠርከው ሚዛናዊ ኃላፊነት ጋር እንድኖር እርዳኝ፡፡