እምነት ያድጋል

እምነት ያድጋል

ሐዋሪያትም ጌታን፡- እምነት ጨምርልን አሉት፡፡ ሉቃ 17 5

ብዙ ሰዎች ምናልባት አንተም ብትሆን ትልቅ እምነት እንዲኖራቸው ትፀልዩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እርሱ በፀሎት ብቻ የሚመጣ አይደለም፡፡ በታዛዥነት እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን ስናደርግና እርምጃ እየወሰድን ስንመጣ ጥቂት በጥቂት የምገነባ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምናልባት ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ስለ ጉዳዩ ልምምድ የሌለን ነገር ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስላልገባን ነገር እንድናደርግ ወይም እንድንሄድበት ሊያዙን ወይም ሊጠይቀን ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ እርምጃ መውሰድ ስንጀምር ስለ እግዚአብሔር ታማኝትና የእኛ እምነት እያደገ መምጣቱን እንለማመዳለን፡፡

እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ለተለየና ለተወሰነ ጉዳይ የእምነት ስጦታ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እምነት ብዙውን ጊዜ የሚያድገው በሕይወት ልምምድ ነው፡፡ የእኛ እምነት በጥልቀት የሚያድገውና የሚጠነክረው እንዲሁም ታላቅ የሚሆነው ስንለማመደው ነው፡፡ በዛሬ የዕለቱ ጥቅሳችን ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን እምነት እንዲጨምርላቸው ጠየቁ፡፡ እርሱም በሉቃስ 17 16 ላይ ያለውን ሃሣብ በማስረዳት ባላቸው እምነት ላይ እንዲሰሩበትና በዚያው እምነታቸውን እንደሚያድግ ገለፀላቸው፡፡

ዛሬም እንደዚያው ጊዜ እምነታችንን የምንገልፅት ነገሮችን በእምነት በማድረግ ነው፡፡ እምነት ሁልጊዜ ድርጊት ይፈልጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር እርሱን እንድንጠብቅና በእኛ ጉዳይ እርሱ ለሚሠራው እንድንተውለት የምፈልግበት ጊዜያቶች አሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ እምነታችንን መፈተን ያለብን እኛው ነገሮችን በማድረግ ነው፡፡ በእምነታችን ለማደግ ስንፈልግ ነገሮችን በትዕግሥት ተስፋ በማድረግና እንደእግዚብሔር ቃል እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡ ነገር ግን ምንም እንቅስቃሴና እርምጃ የማንወስድ ከሆነ እምነታችን አያድግም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እምነትህን በሚያሳይ መንገድ ነገሮችን አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon