ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው፡፡ ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡ – መዝሙረ ዳዊት 62፡1-2
አንድን ላስቲክ የሆነ ነገር ላይ እጠመጥማለሁ ብላችሁ ይበጠስና ሌላ ምትክ ማግኘት ስላልቻላችሁ አንዱን ጫፍ ከሌላው ጫፉ በማሰር ለመጠገን ሞክራችሁ ታውቃላችሁ?
አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ልክ እንደዚህ ላስቲክ ከአቅማችን በላይ እንለጠጣለን እናም ተበጥሰን እንቀመጣለን፡፡ ነገሮችን በድጋሚ ወደቦታቸው በመመለስ መፍትሄ የምናገኝ ይመስለናል ከዚያ ግን ወዲያውኑ ቀድሞ የነበርንበት ችግር ውስጥ እንዘፈቃለን፡፡
ከሆነ ጊዜም ቡሃላ ከጭንቀት ብዛት ህወታችን ልክ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ላስቲክ መሆን ይጀምራል፡፡ ይህም ፈፅሞ ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርገናል፡፡
በህይወታችን ውስጥ የተቀመጠውን የእግዚያብሔርን ህግ እና ልክ ቸል ማለት ህይወታችንን ድካምና መዛል ውስጥ ይከተዋል፡፡ በቀላሉ አዕምሯችሁም እንዲሰራ ማድረግ ይሳናችኋል፡፡ ነግርግን እግዚያሔር እንዲህ አይነቱን ህይወት እንድንኖር ፈቃደኛ አይደለም፡፡
አመለካከታችሁን ከእግዚያብሔር ጋር አጣጥሙ፡፡ ሰላሙን ለራሳችሁና ለህይወታችሁ ፈልጉ፡፡ ሰውነታችሁን አክብሩ ፣ ጤናማ ህይወትን ትልቅ ዋጋ እንዳለው ስጦታ ተመልከቱት። ደስተኛ ሆናችሁ መኖር እንድትችሉ እግዚያብሔር የሰጣችሁን ህይወት በከንቱ አታባክኑት፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚያብሔር ሆይ ፤ በአንተ ውስጥ ማረፍን እሻለሁ፤ በድባቴና በጭንቀት እራሴን ደጋገሜ ከማስመታት እንድወጣ የአንተን ሰላምና እረፍት በህወቴ መከተል እሻለሁ፡፡