እራስህን ለእግዚአብሔር በማቅረብ እረፍ

እራስህን ለእግዚአብሔር በማቅረብ እረፍ

አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፡፡ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡ በፍቅሩም ያርፋል፡፡ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል፡፡ ሶፎ 3÷17

ሰዎች ዛሬ የሚጋፈጡት ችግር ከሥራ ብዛት ነው፡፡ ጥድፊያ፣ ችኮላ፣ በድካም፣ የተሞላ የሕይወት ዘይቤ፣ የምንኖረው ነው፡፡ መጨናነቅ ከእግዚአብሔር ለመስማት አስቸጋሪ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን የዛሬው ቃል እግዚአብሔር በፍቅሩ እንደሚያረጋጋ ተስፋ ይሰጣል፡፡ አንዱና ዋናው ለራስህ ማድረግ የምትችለው ነገር ቢኖር እራስህ በፀጥታና በዝግታ ቦታ ላይ ማሳረፍ ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ለመስማት ጊዜና ለብቻ መሆን ይጠይቃል፡፡ በእርግጠኝነት እርሱን መስማት ከፈለክ በፀጥታ የቀስታ ድምፅ በፀጥታ ውስጥ መሆን አለብህ፡፡ የሆነ ቦታ በመሄድ ለብቻህ ከእርሱ ጋር መሆን ይጠበቅብሃል፡፡ ኢየሱስ ‹‹ወደ እልፍኝህ ግባና በርህን ከውስጥ ዝጋ›› አለ፡፡ (ማቴ 6÷6 ተመልከት) ለጥቂት ደቂቃዎች ሁልጊዜ በሠላምና በፀጥታ ሳትሆን ሥራህን አትጀምር፡፡ እግዚአብሔር ለመፈለግም ደግሞ ጥቂት ረዘም ላለ ጊዜ በጠጥታ መሆን ይጠይቃል፡፡ ትኩረትን ከሚስቡና ከሚረብሹ ነገሮች በመራቅ በእግዚአብሔር ፊት ጊዜ ማሳለፍ መቻል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻህ ስትሆን ስለ ችግርህ አታስብ፡፡ ስለ እርሱ ጥበብና ብርታት ጠይቅ፡፡ እንዲበረታና እንዲያስደስትህ ጠይቅ፡፡

  • እርሱ ለአንተ ሕይወት ያለውን ለማወቅ የምትፈልገውን ጠይቅ፡፡
  • አንተ እንድትሠራ የሚፈልገውን እንዲነግርህ ጠይቀው፡፡
  • አንተ እንዳታደርግ የምፈልገውን እንዲነግርህ ጠይቀው፡፡
  • እራስህን ለእግዚአብሔር በማቅረብ እግዚአብሔርን አድምጥ፡፡

ወደ እርሱ በመሄድህ እርሱን ታከብረዋለህ፡፡ ከእርሱ ለጥያቄህ መልስ ታገኛለህ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻ በምትሆንበት ጊዜ ድምፁን እየሰማህ ካልሆነ አንተ ተናገረው (ጠይቀው)፡፡ በጉዳዩ አትጨነቅ አንተ በበኩልህ የድርሻህን ተወጥተሃልና እርሱ ደግሞ በሕይወትህ መንገድ ይመራሃል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ለመውሰድ ጊዜ አጥተህ ከተጨናነቅህ በእርግጥም አንተ በጣም ጭንቀታም ሆነሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon