
ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኖአልና፣ ሮሜ 8 29
በዛሬው ጥቅስ መሠረት በእኛ ሕይወት የእግዚአብሔር ዓላማ ኢየሱስን እንድንመስል ነው፡፡ እርሱ የሚፈልገው በሃሣባችን፣ በቃላችን፣ ሌሎችን ሰዎች የምንቀበልበት ወይም የምናስተናግድበት መንገድ፣ በግል ሕይወታችን፣ በድርጊታችን ኢየሱስን እየመሰልን እንድንቀጥል ነው፡፡ ኢየሱስን የመምሰል ሕይወት በአንድ ጀምበር የሚሆን ሳይሆን መርጠን የምንቀበለው የሕይወት ሂደት ነው፡፡
የትላንትናው ጥቅስ አስታውስ ሮሜ 12 1 ‹‹እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራሄ እለምናችኋለሁ…›› ለእግዚአብሔር እራሳችንን በጥንቃቄ እራሳችንን አሳልፈን መስጠት አለብን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ነፃ ፈቃድ ሰጥቶናል፡፡ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ብቻ መሆን የሚችልበት መንገድ እራሳችንን በፈቃዳችን ለእርሱ ስንሰጥ ብቻ ነው፡፡ እርሱ እንድንወደው ወይም እንድናገለግለው አያስገድደንም፡፡ እርሱ ይናገረናል፣ ይመራናል፣ ያነሣሣናል፡፡ ነገር ግን ውሳኔን አሳልፎ ለእኛ ይሰጣል፡፡
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ፈጠረ እንጂ ሮቦቶችን አይደለም፡፡ ስለዚህ እርሱ እኛ የምንተገብረውን የተወሰነ መንገድ ሊቀይስልን የሚሞክር ሳይሆን የእራሳችንን ምርጫ እንድናደርግ ነፃነት ሰጥቶናል፡፡ እርሱን እንድንመርጠው ይፈልጋል፡፡ ሕይወታችንን በፈቃደኝነት በእርሱ ፊት በየቀኑ እንድንኖር በመፈለግ እንዲህ ይላል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተ ፍቃድ ይሁን የእኔ ፈቃድ አይደለም፡፡›› ያ በጣም አጭር፣ ቀላል ፀሎት እጅግ በጣም ኃይለኛ በእርግጥ ከልባችን ያልሆነ ከሆነ እጅግ በጣም ኃይለኛ ነው፡፡ እግዚአብሔር የምፈልገው ዓይነት እራሱን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እራስን መስጠት ይወክላል፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ከተናገረ ወይም ስለአንድ ጉዳይ ከአንተ ጋር ሃሣብ ካለው ፈጥነህ ሳትዘገይ እንድትወስን አበረታታሃለሁ፡፡ ድምጹን ለመታዘዝ በመምረጥ ዛሬውኑ ወስን፡፡ ብርታትህ እንዲሆን ጠይቀው እናም በእርሱ በኩል ሁሉን ማድረግ እንደምትችል አስታውስ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እራስህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ በመስጠት ምረጥ፡፡