እርሱ በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ ሥራውን መሥራት ይፈልጋል

እርሱ በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ ሥራውን መሥራት ይፈልጋል

«… በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና» (ሮሜ 8፡14)።

በመንፈስ ቅዱስ መመራት ማለት በትልቁም ሆነ በትንሹ በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ውሳኔ ውስጥ እርሱ እንዲሠራ መፍቀድ ማለት ነው። እርሱ በሰላምና በጥበብ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል በኩል ይመራናል። እርሱ በልባችን ውስጥ በተረጋጋ፣ በትንሽ ድምጽ ወይም እኛ ብዙውን ጊዜ እንደምንናገረው «በውስጥ ምስክርነት» ይናገራል። እኛ በመንፈስ ቅዱስ መመራት የምንፈልግ ከሆነ በውስጥ ምስክርንት እርሱን መከተልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መማር ያስፈልገናል።

ለምሳሌ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ራሳችንን ካዘጋጀንና ስንጀምር በውስጣችን ምጮት ላይሰማን ይችላል። በዚህ ጊዜ ማናልባት ንፈስ ቅዱስ ንግግራችንን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንድንቀይር ውም ዝም እንድንል እያነቃን ሊሆን ይችላል። እንድን ነገር እንደሚገዛ ሰው ዓይነት በውስጣችን የሚመች ስሜት ባይሰማን ህ ያልተመችን ነገር መለየትና መቆየት ይጠበቅብናል።ምናልባት ሌላ ዕቃ ለመግዛት አያስፈልገንም ይሆናል ወይም ወደ ሌላ ቦታ ሄደን ይንኑ ዕቃ የሚሸጥበት ሌላ ቦታ መፈለግ አለብን። ወይም ንን ዕቃ ለመግዛት ትክክለኛው ጊዜ ልሆን ይችላል።ለምን ለሚለው ጥያቄ ሁልጊዜ ትክክለናውን መልስ አናገኝምና ስለዚህ በቀላሉ መታዘዝ ብቻ ያስፈልገናል።

አንድ ጊዜ ወደ አንድ ጫማ መሸጫ መደብር የሆነው ትዝ ይለኛል። የተለያዩ ብዙ «ጥንድ ጫማዎን ለለሞከር መረጥኩ» በድንገት ግን በጣም የማይመች ነገር ገጠመኝ። ህ የማይመች ሁኔታ በውስጤ መንፈስ ቅዱስ «ከዚህ መደብር ውጪ» የሚለውን ድምጽ እስከምሰማበት ጊዜ ድረስ በውስጤ ጨመረ። ለዴቭ ከዚህ መሄድ አለብን አልኩትና ከዛ ወትተን ሄድን። ለምን እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ ማወቅም አልፈልግም። ምናልባትም እግዚአብሔር በመንገዴ ላይ ከሚመጣ አንዳንድ ጉዳት ከሚያመጣ ነገር ሊያተርፈኝ ይሆናል። ወይም ምናልባት በመደብር ውስጥ ያሉ ሰዎች አንዳንድ ከስነ ምግባር ወጪ የሆነ ነገር ሊያደርጉኝ ይችሉ ይሆናል። ምናልባትም ይህ መታዘዜ የሚፈተንበት ሊሆን ይችላል። አስቀድሜ እንዳልኩ አንዳንዴ እግዚአብሔር በተለየ መንገድ ሲመራን ሁልጊዜ ለምን የሚለውን ምክንያት ልናውቅ አንችልም ይሆናል። እኛ ድርሻ ዝም ብሎ መታዘዝ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ እግዚአብሔርን ከምናከብርበት ትልቁ መንገድ እርሱን ድምጹን ሰምተን መታዘዝ ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon