እርሱ በየትም ሥፍራ ይመራሃል

‹‹ … ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።›› (ዮሐ. 21፡15) ፡፡

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢየሱስ ጴጥሮስን ሲጠይቀው እንመለከታለን፤ ‹‹ትወደኛለህን? ›› በእርግጥ ኢየሱስ ጴጥሮስን ይህን ጥያቄ ሲጠይቀው በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ጠየቀው፡፡ በሶስተኛው ላይ ጴጥሮስ ይህን ተመሳሳይ ጥያቄ ኢየሱስ ሲጠይቀው አዘነና እንዲህ አለው ‹‹ አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተም ታውቃለህ›› አለው፡፡

ከዚያም በዮሐ.21፡18 በእርግጥ ጴጥሮስ ይወደው እንደሆነ ለምን ኢየሱስ እንደጠየቀው እናገኛለን፡፡ በእርግጥ ጴጥሮስ የሚወደው እንደሆነ ለምን ኢየሱስ ለመጠየቅ እንደፈለገ ምክንያን እናገኛለን፡፡ ‹‹ … እውነት እውነት እልሃለሁ፥ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል አለው››። እግዚአብሔር በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ብዙ ተገዳደረኝ፤ ምክንያቱም እኔ የራሴ እቅድና በራሴ መንገድ የምጓዝ ስለነበር ነው፡፡ እኛ በእውነት ፍጸጹሙን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንፈልግ ከሆነ እርሱ ምናልባት እኛ ማድረግ የማንፈልጋቸውን ነገሮች እንድናደርግ ሊጠይቀን ይችላል፡፡ በእውነት እርሱን የምንወደው ከሆነ እርሱ እንድናደርገው የነገረንን ነገር ማድረግና የእርሱን መንገድ በህይወታችን እንዲያደርግ መፍቀድ አለብን፡፡

ኢየሱስ ከዮሐ. 21፡18 ቃሉን ሲናገር ሊያሳየን የነበረው አዲስ ክርስቲያን ሳለን አሁን ካለንበት ያነሰ ብስለት ነበረን፡፡ ደስ ወዳሰኘን ሥፍራ ሁሉ እንሄድ ነበር፡፡ እንደ ህጻን ክርስቲያን ማድረግ የምንፈልገውን እናደርግ ነበር፡፡ ነገር ግን በበሰልንና ባደግን ጊዜ ለእግዚአብሔር ለመማረክ እጃችንን ወደ ላይ እንዘረጋለን፤ መሄድ አንኳን ወደ ማንፈልገው ሥፍራ ቢሆን ለመሄድ እርሱን እከተለዋለን፡፡ እርሱ ሊመራህ ወደፈለገው ሁሉ አሁን ፈጥነህ እርሱን ተከተል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ምንም እንኳን ወደየት እንደሚመራህ ባታውቅም ዛሬ ወደ ዘለዓለማዊውን ‹‹አወንታ›› ለእግዚአብሔር ለመናገር ትፈልጋለህ፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon