እርስ በራሳችሁ ተበረታቱ

እርስ በራሳችሁ ተበረታቱ

ለፍቅር እና ለመልካም ሥራ እንድንቃቃ እርስ በራሳችን እንተያይ – ዕብራዊያን 10፡24

ሶስት ጓደኞች አሉኝ አንዳድ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ቡና እጠጣለሁ ምሳም እበላለሁ፡፡ አልፎ አልፎ እግዚአብሔር በውስጣችን ስላሰቀመጣቸው ነገሮች ወይም ለሌሎች ማድረግ ስለምንፈለግው ወይም ደግሞ ፈጠራ ስለታከለባቸው ሀሳቦች እናወራለን፡፡ ይህን መሰል ንግግሮች እግዚአብሔርን እንደሚያስደስተው አምናለሁ፡፡

ሰዎች መልካም በማድረግ ብርቱዎች እንዲሆኑ ማነሳሳት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ዕብራዊያን 10፡ 24 ለፍቅር እና ለመልካም ሥራ እንድንቃቃ እርስ በራሳችን እንተያይ ይላል፡፡ በእርግጥ ሌሎች ለመልካም ሥራ የተነቃቁ እንዲሆኑ ለማነሳሳት ማጥናት ይገባናል፡፡

እግዚአብሔርን በግል መከተል ታላቅ ነገር ነው ይሁን እንጂ ከወዳጆቻችን ጋር እርሱን መከተል በጣም አስደሳች ነው፡፡ ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸውን ጌታን የሚከተሉ ሰዎች ፈልጋችሁ በጋራ አቅዱ ፣ ጤናማ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመምራትም እንድትለማመዱ አበረታታችኋለሁ፡፡ ከእነርሱም ጋር ጌታን እንድታገለገሉና በፍቅሩም አንድነት እንዲኖረችሁ አድርጉ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከትክክለኛ አንተን እንደከተል ከሚያደርጉኝ ወዳጆች ጋር አገናኘኝ ፤ የክርስትናን ሕይወት ከሌሎች ሰዎችም ጋር አብሬ እርስ በራሳችን በአንተ ፍቅር እየተነሳሳን መኖር እፈልጋለሁ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon