“እቅጩን መናገር”

“እቅጩን መናገር”

በቃል ብዛት ዉስጥ ኀጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነዉ፡፡ – ምሳሌ 10:19

ኛ ሁላችን ለቃሎቻችን እንዴት ድንበር ማበጀትና መቀጠል እንዳለብን መማር ያስፈልገናል፡፡ ምሳሌ 10፡19 በቃል ብዛት ዉስጥ ኀጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነዉ፡፡ ይላል፡፡ ቤላ ቋንቋ ብዙ የሚናገሩ ሰዎች ራሳቸዉን አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ያገኛሉ ማለት ነዉ፡፡

ቃሎቻችን ብዙ ሐይል ስለሚሸከሙ እኔና እናንተ መባል ያለበትን ብቻ ማለትን መማር ያስፈልገናል፡፡ ይህንን ነገር “ጥሩን መናገር” ብዬ መጥራት እወዳለሁ፡፡ ክፊያ ስናገኝ አብዛኛዎችችን የሚደርሰንን የተጣራዉ ክፊያ ነዉ፡፡ ከዉስጡ መወሰድ ያለበት ሁሉ ከጠቅላላዉ ክፊያ ተወስዷል፡፡

እኛም ቃሎቻችንን በተመለከተ ተመሳሳይ መርህ መተግበር እንችላለን፡፡ ከአንደበት ከመዉጣታቸዉ በፊት አላስፈላጊ ቃላትን ከንግግራችሁ ማስወገድ አለባችሁ፡፡ ይህ የሚያካትተዉ አሉታዊ ንግግርን፣ አሉባልታን፣ ከአንገት በላይ ሽንገላን፣ ከርዳዳ ፌዞችን ወይም አጓጉል ቀልዶችንም ነዉ፡፡ በምትኩ ስለሌሎች መልካምን አዉራ፣ መልካም ጎኖቻቸዉን ፈልገህ እሱ ላይ አትኩር፤ እነርሱ ይበረታታሉ አንተም ራስህን ችግር ዉስጥ አታገኝም፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! “ጥሩ ነገር እንዳወራና” ከችግር እንድላቀቅ ዘንድ እፈልጋለሁ። አንተ ለቃሎቼ ባበጀሀዉ ወሰን መኖር እንድችል አጠንክረኝ አበረታታኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon