እባክህ ፀጥ በል

ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ አሳብህም ትጸናለች፡፡ ምሣ 16 3

እግዚአብሔር በሕይወታችን ጣልቃ የሚገባው እኛ ስንጠይቀው ነው፡፡ እኛ የራሳችንን ነገር በራሳችን መንገድ ለማድረግ መሞከርን ስናቆም እርሱ በነገሩ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር በጥልቀትና በኃይል መናገር የሚጀምረው መቼ ነው; እኛ መናገር በማቆም መስማት (ማዳመጥ) ስንጀምር ነው፡፡ የእራሳችንን ችግር ለማቃለል ከመሞከር ይልቅ በመጨነቅና የተለያዩ ዘዴዎችን ከመፈለግ እግዚአብሔር የሚለውን በፀጥታ ማዳመጥ አለብን፡፡

የዛሬው ጥቅስ ብዙውን ጊዜ የእኛን ‹ሥራ› ይዘረዝራል፡፡ የእኛ ሥራ በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ‹‹ሥራ›› ናቸው፡፡ የእኛ ማሳበብ፣ የእኛ ምዘና (ትንታኔ)፣ የእኛ ሙከራ ማድረግ በሚገባን ወይም እየተደረገ ያለውን የእኛ ስሌት ነው፡፡ እግዚብሔር ያለው የእራሳችንን ሥራ ለእርሱ እንድናስረክብ የእኛ ሃሣብ ይገነባል፡፡ በሌላ አገላለጽ አእምሮአችንን በማረጋጋት ፀጥ ማድረግ ካልቻልን ብሩህ አእምሮ ስለሚኖረን እግዚአብሔርም ይናገረንና የሚሻልን የአሰራር አቅጣጫ ሃሣቦችን ይሰጣል፡፡

አንድ ወቅት ለገጠመኝ ችግር ምንም መልስ ላጣሁበት ችግር ሕይወቴ ተመሰቃቀለና ትርጉም አጣብኝ፡፡ በመጨረሻ ጠጥ በማለት እግዚአብሔርን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ስጠይቀው እርሱም በቀላሉ ‹‹አንድ ሰው በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምክር ቢጠይቅሽ የምትመክሪውን ዓይነት እርምጃ ውሰጂ አለኝ፡፡›› በመሠረቱ ማድረግ ያብኝን አውቅ ስለነበር ወዲያው ሰላሜ ተመለሰልኝ፡፡ እኛ ፀጥ ብለን ካደመጥነው እግዚአብሔር ለእኛ መልስ አለው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አእምሮህና አንደበትህን ፀጥ አድርገህ እግዚአብሔር ይናገርህ ሃሣብህ የፀና ይሆናልና፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon