“እነርሱ” አንተና እኔ ነን

የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ ነው ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ። – መዝ 89፡14

ግዚአብሔር ፍተሃዊ ነዉ፡፡ ይህ ባህሪዉ ነዉ፤ ማንነቱ እና እኛም እንድንከተለዉ የሚፈልገዉ ባህሪዉ፡፡

ፍትሕ ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን ማስተካከል ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በዓለም በዙሪያችን ያለዉን ኢ-ፍትሓዊነት ለማስተካከል በእኛ በኩል የምሰራለት አስፈጻሚዎቹ ነን፡፡ ዘወትር ትክክል ያልሆነ ነገር ስናይ የመጀመሪያዉ ምላሻችን ስለዚያ ነገር መጸለይ መሆን አለበት፡፡ ሁለተኛዉ ምላሻችን ደግሞ ራሳችንን “እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብሎ መጠየቅ መሆን አለበት፡፡

በዙሪያችን ያለዉን ፍላጎት ስንመለከት በስሜት መጎዳት ቀላል ነዉ ስለዚህ ዙሪያችንን ስናይ ይህ የተወሰነ ሰዉ ችግር ነዉ “እነርሱ” ችግሩን መፍታት እንዲችሉ “እነርሱ” ያንንና ይህንን ቢያደርጉ ብለን እንመኛለን፡፡

“እነርሱ ማን ናቸዉ” ብለህ ጠይቀህ ታዉቃለህ? እኔ እንደማስበዉ “እነርሱ” እኛ ነን፤ አንተና እኔ! ሁሉን ነገር ማድረግ አትችል ይሆናል ግን ጥቂት ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡ እ-ፍትሃዊነትን አይተህ ምንም ሳተደርግ አትቅር፡፡ እግዚአብሔር አንተን አንቅስቃሴ አልባ እና አሳላፊ እንድትሆን አልፈጠረህም ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለብህ እንዲጠቁምህ እርሱን እንድትጠይቀው ነው የሚፈልገው፡፡ አንተን የፈጠረህ ለመነሳሳት፣ ለቅንነትና ለመልካም ጉጉት ነዉ፡፡ ጥቅም እንዲዉሉ፣ እርሱን እንዲያከብሩና ሰዎችን እንዲጠቅሙ በአንተ ዉስጥ ስጦታዎችን አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ፍትሃዊ ኑሮ ኑር፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ በዙርያዬ ያለዉን እ-ፍትሓዊነት እያየሁ አንድ ነገር ማድረግ ስችል “እነርሱ” ይህንንና ያንን ቢያደርጉ ብዬ እንድጠቁም አትፍቀድልኝ፡፡ በሞገስህ ሙላኝ በዙርያዬ ያለዉን ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳስተካክልም መንገዱን አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon