በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ፣ ከማህፀን ሳትወጣ (የተመረጠ ባሪያዬ አድርጌ) ቀድሼሃለሁ፤ ለአህዛብ ነብይ አድርጌሃለሁ፡፡ – ኤር 1፡5
እግዚአብሔር እንዳዘነባችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል? እስከሆነ ግዜ ድረስ ‹‹ጆይስ፣ አንቺ ለእኔ ድንገት የተከሰትሽ አይደለሽም፤ ሳገኝሽ፣ ማን ልትሆኚ እንደምትችይ ቀድሜ አውቅ ነበር፡፡›› ብሎ እግዚአብሔር እኔን ከመናገሩ በፊት ሊያዝንብኝ እንደሚችል ተሰምቶኝ ያውቃል፡፡
እስቲ ስለዚህ አስቡ! ከመነሻው መጨረሻውን ያውቃል፤ እያንዳንዱን የሕይወታችን ቀናችንም በመፅሃፉ ተፅፈዋል፡፡ መጥፎ ይሁን ጥሩ፣ እያንዳንዱ የምንወስነውን ውሳኔ በዚህ ምድር ከመምጣታችን በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ ያውቃቸዋል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአፋችን ወጥተው ያልተነገሩ ገና የሚነገሩ ቃላትን ያውቃቸዋል፡፡ ከ አንድ አመት ቡሃላ እንኳን ልንናገር የምንችለውን ነገር ያውቃል።
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ሁልጊዜ በእኛ ላይ በጣም ያዝናል ብለን እናስባለን፡፡ ስሕተት ማድረጋችን እውነት ነው ፤ ልንደሰትበትም አይገባም – በቁም ነገር ልንይዘው ይገባል፡፡ በዚህ ውስጥ ሁሉ ብናጠፋም፣ ከእርሱ ጋር ተጣብቀን እስከኖርን ድረስ እግዚአብሔር ለእኛ ተስፋ አለው፤ ሊለውጠን እንደሚችል ያውቃል፡፡
እግዚአብሔር አያዝንብንም፤ በሚያስጨንቀን ነገር ሁሉ ላይ ለእኛ ሙሉ ተስፋ አለው፤ እኛ በራሳችን ላይ ካለን እምነት በላይ እርሱ በእኛ ላይ እምነት አለው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! አንተ ለእኔ ያለህ ተስፋ አበረታችና ለተሻለ ነገር የሚያነቃቃ ነው፡፡ በራሴ ላይ እንኳን እምነት ሳጣ፣ አንተ ግን ታምነኛለህ፤ ይህም ስህተቶቼን አልፌ እንደሄድና እንድከተልህ ብርታትን ይሰጠኛል፡፡