እናንተ ስትደክሙ እርሱ ብርቱ ነው

እናንተ ስትደክሙ እርሱ ብርቱ ነው

እርሱ ግን፣ጸጋዬ ይበቃሀል፤ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና አለኝ፡፡ስለዚህ የክርስቶስ ኃይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ፡፡ – 2 ኛ ቆሮ 12፡9

ካማ ወይስ ብርቱ? ራሳችሁን ለመግለጽ ከእነዚህ ቃላት አንዱን መምረጥ ቢኖርባችሁ የትኛውን ይሆን የምትመርጡት? ብዙዎቻችን የምንለው “ደካማ” ይመስለኛል። ነገር ግን በድካሞቻችን ተሸንፈን መቅረት እንደሌለብን ታውቃላችሁ?

ድካማችሁን ለማሸነፍ መንገዱ በእግዚአብሔር ጥንካሬ ላይ መደገፍ ብቻ ነው፡፡ይህንን ለማድረግ በራሳችሁ ድካም ላይ ማተኮራችሁን ማቆም አለባችሁ፡፡ያልሆናችሁትን ነገር ሁሉ መመልከት አትችሉም፡፡እግዚአብሔር የሆነውን ነገር ሁሉ መመልከት አለባችሁ፡፡በእርሱ ጥንካሬ እና ሊያደርግላችሁ በሚፈቅደው ነገሮች ላይ አተኩሩ፡፡

የአለም ድካም የእናንተ ውርስ አይደለም፡፡ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው፣በመስቀል የሞተው፣በሶስተኛውም ቀን የተነሳው እናንተ ደካማ እና ተሸናፊ ሆናችሁ እንድትኖሩ አይደለም፡፡በዛ ሁሉ ያለፈው ለእናንተ ውርስ፥በዚህ ህይወት ስልጣን፥ እና ለሚያጋጥሙን ሁኔታዎች የሚሆን የሱን አቅም ለመስጠት ነው፡፡

ባቃታችሁ በማናቸውም ስፍራ እግዚአብሔር ጥንካሬውን ሊሰጣችሁ ዝግጁ ነው፡፡ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከድክመታችሁ ጋር ስትጋፈጡ፣ ቢደክማችሁ እርሱ ግን ብርቱ እንደሚሆን አስታውሳችሁ አውጁ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ደካማ ስሆን አንተ ብርቱ እንደሆንክ በአፌ እየተናገርሁ አውጃለሁ፡፡ስለዚህ በድካሜ ተነሳ አልጨነቅምም አልሸነፍምም፡፡ይልቁንስ በአንተ ጥንካሬ ላይ እምነቴን አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon