እንደ ሥጋ የሚኖሩ ልባቸውን በሥጋ ፍላጎት ላይ ያሳርፋሉ፤እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን ልባቸውን በመንፈስ ፍላጎት ላይ ያደርጋሉ፡፡ – ሮሜ 8፡5
እንደ አማኞች አስተካክሎ ማሰብ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ያለእርሱ መኖር አንችልም፡፡ ልክ እንደ ልብ ትርታችን አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አብዛኞቹ በህይወታችን የሚያጋጥሙን ችግሮች በተሳሳተ አስተሳሰብ ውስጥ ስር የሰደዱ ናቸው እንጂ በእውነት ላይ የተመሰረቱ አይደሉም፡፡
ትክክለኛ አስተሳሰብ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት እና ቃሉን በማጥናት የምናደርገው መደበኛና የግል ህብረት ውጤት ነው፡፡ አስተሳሰባችን ፍሬን ስለሚያፈራ አስተሳሰባችን እስኪስተካከል ድረስ ህይወታችን እንደማይስተካከል እውነታውን መቀበል ለእኛ አስፈላጊ መሆኑን ወደ መረዳት መምጣት አለብን፡፡ እኔ እና እናንተ መልካም አስተሳሰብ ስናስብ ህይወታችን መልካም ፍሬ ያፈራል፡፡ መጥፎ ሀሳብ ስናስብ ህይወታችን መጥፎ ፍሬ ያፈራል፡፡
እግዚአብሔርን ለረጅም ጊዜ ባገለገልኩና ቃሉን ባጠናሁ ቁጥር በአዕምሮዬ ውስጥ የሚካሄደውን ማወቅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተረድቻለሁ። አዕምሮው በሄደበት ሰውየው ይከተላል፡፡ ቀጣይነት ባለው መልኩ አስተሳሰባችንን መቆጣጠር ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አስማምተን ለመቀጠል እና ከጠላት ጋር ያለብን ጦርነት ለማሸነፍ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ትክክለኛ አስተሳሰብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ አሳይተኸኛል፡፡ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ አንተን እፈልግሀለሁ ቃልህንም አጠናለሁ፡፡