እንደ ተቃውሞው ትልቅነት እድላችንም ይተልቃል

እንደ ተቃውሞው ትልቅነት እድላችንም ይተልቃል

በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል። – 1 ቆሮ 16፡9

እግዚአብሔር ለሕይወታችን አዲሰ ሀሳብ በልባችን ውስጥ ሲያስቀምጥ ወይም አንድ ሕልም ፣ ራዕይ ወይም አዲስ ትግል ለሕይወታችን ሲሰጥ ጠላትም በታውሞ መገኘቱ አይቀርም፡፡

እግዚአብሔር በዘለቄታው ወደ አዳዲስ ደረጃዎች ይጠራናል፡፡ አንዳንዱ ትልቅ እና ጠቀሚ ሌሎችም ደግሞ በአንጻሩ ያነሱ እና ጥቅም የሌላቸው ይመስላሉ፡፡ ምንም ዓይነት ቢሆን ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን ወደ አዲስ ደረጃ ስንደረስ ከጠላታችን ከሰይጣን የሚሰነዘሩ አዳዲስ ተግዳሮቶችን ጋር እንፋጠጣለን፡፡ ከተግዳሮቱ ጎን ለጎን እድሎች ይመጣሉ፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና ለፍርሃት ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን እኛ ትልቅ የሚመስለን ነገር በእርሱ የሚቻል ነው፡፡ ጌታ በምንም አይደነቅም ምንም የሚፈራው ነገር የለውም፡፡ ከእርሱ ጋር ሆነን ከፊታችን ያለና የማንደረስበት እድል የለም፡፡

እግዚአብሔር ወደ ጠራህ አዲስ ደረጃ ለመሄድ ቁርጠኝነት ካለህ ከፊትህ ባለህ ተግዳሮት ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ባይሆን የተቃውሞ ብርታት ከፊት ለፊትህ ያለውን እድል ትልቅነት ነው፡፡ በርታ ፣ ደፋርም ሁን ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ጽናት ዘወትር ካንተ ጋር ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በሰልፉ መሀል እንዳልዝል እርዳኝ፡፡ ለእኔ ታላቅ እቅድ እንዳለህና በውስጡ ታላቅ እድል ፈንታ ያለው ሰልፍ እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ በአንተ እታመናለሁ፡፡ ወደ ሚቀጥለው የእምነት ደረጃ እና ሌሎችን በፍቅር ማገልገል ወደ ምችልበት አድርሰኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon