
እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። – ዕብ 12፡2
ብዙ ጊዜ ማንኛውም ነገር ሁለት ገጽታ አለው፡፡ መስቀሉም እንዲሁ የስቅለትና የትንሳኤ ገጽታ አለው፡፡ ኢየሱስ ሌላኛውን ገጽታ ለማግኘት አንደኛውን ገጽታ መታገስ ወይም መጽናት ነበረበት፡፡ ባይጸና ኖሮ ሁላችን ያለ አዳኝና ኃጢያታችን ሳይሰረይልን እንቀር ነበር፡፡
ዕብራዊያን 12፡2 እንዲህ ይላል፣ ‘’ኢየሱስ የመስቀሉን የሌላኛ ገጽታ የሆነውን ደስታ ለማግኘት (ትንሳኤውን) ሲል የመስቀሉን ህመም ታገሰ፡፡’’ ልክ እንደ ኢየሱስ አስቸጋሪ ነገሮችን መታገስና መጽናት አለብን፡፡ የእኔ ጽናት ትርጓሜ ‘’ሰይጣንን ለመቃወምና ከአንዱ የመስቀል ገጽታ ወደ ሌላኛው ገጽታ ለመግባት መከራ በሕይወታችን ውስጥ መስራት የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እንዲሰራ መፍቀድ ማለት ነው፡፡’’
ባልጠበቅነው ሁኔታ ብንመታ፣ ለሰራነው መጥፎ ስራ መከራ ብንቀበል ወይም መልካምን በማድረግ ፈተናንና ኃጢያትን በመቃወም በጽናት በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ማለፍ አለብን፡፡ ከዚህ መከራ ጊዜ በኋላ የሚጠብቀንን ሽልማት ማለትም መልካሙን ውጤት በደስታ እንቀበላለን፡፡
ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈተናዎቹን በያዘበት መንገድ ተበረታቱ፡፡ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ እስከ መጨረሻው ታገሰ ጁ፣ ጸና፡፡ እንዲሁ እንደታደርጉ ኃይሉን ሰጥቷችኋል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ኢየሱስ መጽናት እፈልጋለሁ፡፡ ወደፊት የሚጠብቀኝን ሽልማት ማግኘት ያለውን ደስታ በመመልከት በመንገዴ ላይ የሚገጥመኝን ማንኛውንም መከራ በጸጋህ እንድታገስ ዓይኔን ክፈት፡፡