እንደ ኢየሱስ ይቅር ማለትን ተማር

እንደ ኢየሱስ ይቅር ማለትን ተማር

ኢየሱስም ፡- አባት ሆይ ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ፡፡ – ሉቃስ 23፡34

ጠጥቶ አንዲት ሴት እና ልጇን ስለ ገደለ አንድ ታዳጊ ሰምቼ ነበር፡፡ የሴትየዋ ባል ያንን ጎረምሳ ይቅር እንዲል እግዚአብሔር እንደሚፈለግ ያውቅ ነበር ፤ በብዙ ጸሎትም የእግዚአብሔር ፍቅር በሕይወቱ በመፍሰሱ ጉዳት አድራሹን ይቅር አለ፡፡

ይህ ሰው እንደ ኢየሱስ ይቅር ማለትን ያውቃል፡፡ ይህ ታዳጊም እንደተጎዳ እና ፈውስ እንደሚስፈልገውም ተረድቷል፡፡

ሰዎች ሲጎዱን ሰዎቹ ጉዳቱ በእኛ ላይ እንዳደረጉት ሳይሆን በራሳቸው ላይ እንዳደረጉት እንቁጠር ምክንያቱም ሰዎችን መጉዳት ይጎዳልና ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ ሰው ሰውን ሲጎዳ ምናልባትም በዚያው የጉዳት መጠን እራሱንም እየጎዳ በውጤቱም እየተሳቃየ ነው፡፡ ለዚህ ነው ጌታችን በመስቀል ላይ በሕመም ተንጠልጥሎ በነበረበት ወቅት ስለገዳዮቹ ‹‹ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር ›› በላቸው ያለው፡፡

ይህ አስገራሚ ይቅርባይት ነው፡፡ ይህ ያነሳሳችሁ ፡፡ ሁላችንም እንደ ኢየሱስ ይቅር ማለትን መሻት አለብን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ ሰዎች ሲጎዱኝ የኔን ሕመም ትቼ የእነርሱን መጎዳት እንዳይ እንድወዳቸው እና እንደ ኢየሱስ ይቅር እንድላቸው እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon