እንደ እምነትህ

እንደ እምነትህ

ኢየሱስም ለመቶ አለቃ። ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። – ማቴ 8፡13

ከብዙ ዓመታት በፊት ባለፈዉ ህይወቴ በደረሰብኝ ጥቃት ምክንያት እጅግ አሉታዊ ነበርሁ፡፡ በዚህም ምክኒያት ሰዎች እንደሚጎዱኝ ጠበቅሁ እነርሱም አደረጉት፡፡ ሰዎች ታማኝ እንዳልሆኑ ጠበቅሁ እነርሱም አደረጉት፡፡ ምንም መልካም ነገር ይከሰታል ብዬ ለማሰብ ፈራሁ፡፡

ምንም መልካም ነገር እንደማይከሰት በመጠባበቅ ራሴን ከመጎዳት የጠበቅሁ መስሎኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ቃሉን ማጥናትና እግዚአብሔር ህይወቴን እንደሚያድስ ማምን ስጀምር ሁሉም አሉታዊ አስተሳሰቦቼ መወገድ እንዳለባቸው አስተዋልኩኝ፡፡

በማቴ 8፡13 ላይ እንደ እምነታችን እንደሚደረግልን ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ ሁሉም ነገሮች አሉታዊ እንደሆኑ አምኘ ስለነበር በተፈጥሮ ብዙ አሉታዊ ነገሮች በእኔ ላይ ተከሰቱ፡፡ ስለዚህ እምነቴን በእግዚአብሔር ላይ ማኖር ስጀምር፣ እርሱ በህይወቴ መልካም ነገሮችን እንደሚያደርግ ሳምን፣ ከጊዜ በኋላ መልካም አዉንታዊ ዉጤት ተቀበልኩኝ፡፡

በቋሚነት አሉታዊ ነገር እያጋጠመህና ለምን እያጋጠመህ እንደሆነ እያሰብክ ነው? ምንአልባት የተለየ ነገር ማመን መጀመር ይኖርብህ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን መታመንና የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ማመን ጀምር፡፡ ከዚያም ነገሮችን እንደ እምነትህ ሲሰራ ተመልከት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! አሉታዊ ነገሮችን ማስወገድና ለተሻለ ነገር ማመን መጀመር እፈልጋለሁ፡፡ አንተ በህይወቴ  ታላላቅ ነገሮችን እንደምታደርግ በማመን እምነቴን እንዳነሳሳ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon