
“በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” (ሚል.3፡10)፡፡
ብዙ ጊዜ ከሚጸለዩት ጸሎቶች በተደጋጋሚ በብዙ ሰዎች ሲጸለይ የምሰማው ጸሎትና እኔም በራሴ ብዙ ጊዜ የምጸልየው፣እኔ እንዲህ ብዬ እጠራዋለሁ የ “አሁን” ጸሎት እንዲህ ዓይነት ጸሎት ነው። “ጌታ ሆይ አሁን አሁን ስለዚህ ምግብ እናመሰግንሃለን፤” “እግዚአብሔር ሆይ አሁን አንድትጠብቀን እንጸልያለን” “አባት ሆይ ዛሬ ማታ አሁን ወደ አንተ እንቀርባለን” “ኦው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሆይ አሁን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ብትረዳን እናመሰግንሃለን”: ምን እያልኩ እንዳለሁ አስተውላችኋል? ስለብዙ ትላልቅ ነገሮች እግዚአብሔርን መጠየቅ አሳፋሪ እንደሆነ እናስባለን።
“Just” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል «ጻድቅ» ወይም «በቂ» በሚል አቻ ትርጉም ሊተረጎም ይችላል። በተጨማሪም «በጣም ትንሽ ነገር ማግኘት» ወይም «በጠባብ ወይም ለጥቂት» ማለት ይቻላል። እግዚአብሔር ከምንለምነው ወይም ተስፋ ከምናደርገው ወይም ከምንጸልየው በላይና ባሻገር ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ሊያደርግልን ይፈልጋል (ኤፌ.3፡20)። እርሱ የሰማይን መስኮት ከፍቶ በረከቶቹን አትረፍርፎ ሊያፈስልን ይወዳል። እንግዲህ እንዲህ ከሆነ ለምን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን ትንሽ ነገር ለማግኘት እንጸልያለን? ለምን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እጅግ ትልቅ ነበር ለመጠየቅ እናፍራለን? እርሱን በዚህ መንገድ ስንቀርበው እርሱ ቸርና መልካም እንደሆነ አለማመናችን የሚያሳይ ይመስላል። እኛ ይህንን አስረግጠን ማወቅ ያለብን እርሱ «ጥቂት» ነገር ብቻ መጥኖ የሚሰጥ አምላክ እንዳልሆነ ነገር ግን በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሠረት እርሱ አትረፍርፎ ይባርከናል።
እግዚአብሔር በፍርሃት የተሞላ፣ ዋስትና የሌለው «ትንሽ» ጸሎት የመስማት ፍላጎት የለውም። እርሱ የሚፈልገው ድፍርት ያለው፣ አስተማማኝ የሆነ፣ እምነትን የተሞላ ጸሎትን ከእርሱ ጋር አስተማማኝ ወዳጅነት ባላቸው ሰዎች የሚጸለየውን ጸሎት ይፈልጋል።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ወደ ለመጸለይ ስንቀርብ “ትንሽ” ትንሽ በቂ አይደለም።