እንዳትጠፋ የእግዚአብሔር ዓይን ባንተ ላይ ነው

እነሆ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፡፡ በምህረቱም ወደሚታመኑት….. መዝ 33 18

በሕይወቴ አስታውሳለሁ ከእግዚአብሔር ለመስማት በብርቱ እሞክራለሁ ደግሞም እሳሳታለሁ በማለትም በጣም እፈራለሁ፡፡ የዛን ጊዜ ከእግዚአብሔር ለመስማት ገና ሲጀምር አካባቢ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መመራት ለእኔ አድስ ልምምድ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሣ በጣም እፈራ ነበር፡፡ ምክንያቱም ብዙም ከእግዚአብሔር የመስማት ልምምድ ስለሌለኝ በትክክል ከእግዚአብሔር መስማቴንና አለመስማቴን ስለሚያጠራጥረኝ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ስህተቶቻችንን እንደ ልባችን ቅንነት እንዲያድነንና ለመልካም እንዲያደርግልን አልገባኝም ነበር፡፡

እግዚአብሔር የእምነት እርምጃ በመውሰድ አንዳንድ ነገሮችን እንዳደርግ ሊነግረኝ ይፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ ጌታ ሆይ አንተን ባጣህስ; በትክክል ከአንተ ያልሰማው ከሆነስ; ከአንተ በእርግጠኛ ሳልሰማ ቀርቼ ብሳሳትስ; ጌታ ሆይ አንተን አጣለሁ በማለት እፈራለሁ እል ነበር፡፡

እርሱ ግን ‹‹ጀሲ አይዞሽ ከእኔ ጋር ብትተላለፊም እኔ እፈልግሻለሁ፡፡›› ብሎ በቀላሉ ተናገረኝ፡፡ እነዚያ ቃሎች ድፍረት ሰጡኝና እግዚአብሔር ለጠራኝ ነገር ለማድረግ ታላቅ ሰላም በልቤ ተሰማኝ፡፡ እነዚያን ቃላቶች ካሰማው ወደህ በእምነት እርምጃ ለመውሰድ ብዙ ጊዜያት አበረታታኝ፡፡ ዛሬም ደግሞ ይህንኑ ቃላት አሁን እግዚአብሔር ለሚልህ ጉዳይ በእምነት እርምጃ እንድትወስድ ላበረታታህ ለአንተ ላካፍልህና ላበረታታህ እወዳለሁ፡፡

በማንኛውም ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከእግዚአብሔር ድምፅ ሰምተህ ለማድረግ ከወሰንክ የእራስህን እርምጃ መውሰድ፣ ማመን አለብህ፣ ስህተቶች እንኳ ብትሰራ ወደ መልካምነት ይለወጣል፡፡ አንተም ይህንን እድል መጠቀም አለብህ፡፡


የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በምታምነውና ከእግዚአብሔር በሰማው ነገር ከፍርሃት የተነሣ እድሉ ሊያመልጥህ አይገባም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon