እኛ ሁላችን መልካሙን ውጊያ እየተዋጋን ነው

እኛ ሁላችን መልካሙን ውጊያ እየተዋጋን ነው

በውሀ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ወንዙን ስትሻገረው፣አያሰጥምህም፤በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣አያቃጥልህም፤ነበልባሉም አይፈጅህም፡፡ – ኢሳ 43፡2

አንዱ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመን ውሸት ብቻችንን እንደቀረን እና ከሰይጣን ጋር እንደምንዋጋ ነው፡፡ ሰይጣን እኛን ገንጥሎ እኛ እያለፍንበት ባለነው ማንም እንዳላለፈ እንድናስብ ያደርገናል፡፡

እውነታው ግን እኛ ሁላችን ጦርነት ላይ ነን፡፡ የሚደክማችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም፡፡ የሰይጣንን ውሸቶች እና የራሳችሁን ስሜቶች ቆሞ መቃወም የሚደክማችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም፡፡

ልክ እንደ እናንተ መልካሙን የእምነት ውጊያ እኔም እዋጋለሁ፡፡ ሌሎችም ከቁጥር በላይ የሆኑ አማኞች ከእናንተ ጋር ጠላትን ተቃውመው ይቆማሉ፡፡

ከሁሉም የሚበልጠው እግዚአብሔር በመንገዳችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ኢሳ.43፡2 አስቸጋሪ ጊዜያትን እግዚአብሔር እራሱ ከእኛ ጋር ስለሚሄድ እንደምናልፈው ተስፋ ይሰጠናል፡፡ በውሀ ውስጥ ስናልፍ አያሰምጠንም፣በእሳት ውስጥ ስናልፍ አያቃጥለንም ምክንያቱም እርሱ ከእኛ ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ተበራቱ፡፡ ቀጥሉ፡፡ እግዚአብሔር ጥንካሬ እና ጥበብ ለሁሉም ውጊያዎቻችሁ ይሰጣችኋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከጠላት ጋር እየተዋጋን ካለነው ከእኔ እና ከሁሉም ተከታዮችህ ጋር ስለሆንክ አመሰግናለሁ፡፡ ብቻዬን እንደሆንኩ የሚነግረኝን ውሸት አላምንም፡፡ ሁሌም ከእኛ ጋር ለመሆን እና ስንፈልግህ ልትረዳን አንተ ታማኝ ነህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon