«… ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ»(2ኛ ሳሙ. 22፡4)።
ተስፋ በሚያስቆርጥ ጦርነት ፊት ኢዮሳፍጥ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በመጀመሪያ እርሱ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ፣ አስደናቂ፣ ኃይለኛና አስገራሚ እንደሆነ በምሥጋና አወጀ። እግዚአብሔር ለጠራው ህዝብ የገባውን የተስፋ ቃል /ኪዳን/ ለመጠበቅና ህዝቡን ለመጠበቅ ሲል በቀደመው ዘመን የሠራውን የእርሱን ኃይለኛ ሥራዎች የተወሰነውን በመቁጠር ጀመረ። ከዚያ ሁሉ በኋላ ደግሞ የእርሱን ጥያቄ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ። ጌታ የደረሰባቸውን ችግር መቆጣጠር እንደሚችል በእርሱ ላይ ያለውን ሙሉ መታመን በመግለጥ ጀመረ። ከዚያም በቀላሉ እንዲህ አለ « አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ጠላቶታችን የመጡት አንተ በውርስ ከሰጠኸን ርስት ላይ ሊያፈናቅሉንና ሊያባርሩን ለመሞከር ነው። አሁን ይህ ችግር በአንተ ዘንድ ትንሽ እንደሆነ እናገራለሁ። አንተ ግን በጣም ትልቅ ነህ፤ አንተ ይህን ሁኔታ በአንተ ሥር መቆጣጠር እንደምትችል አውቃለሁ» አለ።
ወደ እግዚአብሔር ለእርዳታ ስንጸልይ እርሱ በመጀመሪያ የጸሎታችን ጊዜ ላይ እንደሚሰማን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል። ለምንጸልየው ጸሎት ረጅም ጊዜ በመውሰድ በአንድ የጸሎት ርዕሰ ጉዳይ ደግመን ደጋግመን በመጸለይ ጊዜ ማባከን የለብንም። ስለሚያስፈልገን ነገርና ስለምንሻው ነገር ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እጅግ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁና ከዚያም እንደገና ሃሳቡ ወደ አዕምሮአችን ሲመጣ እርሱን እግዚእበሔር እየሠራ ስላለው ነገር መማስገን ነው። የእርሱ ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን ማወቅ በእርሱም እንደምንታመን ለእርሱ መንገር ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር ማንኛውንም ችግር ከከምጣቱ በፊት አንተን ለመታደግ ዕቅድ አለው። እግዚአብሔርን ምንም ነገር አያስደንቀውም። እርሱ ላይ ማተኮርህን ቀጥል፣ አምልከው፣ አመስግነው፣ ምሥጋና አቅርብለት። የእርሱ እርዳታ በደጅ ነውና። የእርሱን ድምጽ መስማትን ቀጥልበት፤ በሚያጋጥምህ ጦርነት /ተግዳሮቶች/ ውስጥ እርሱ ወደ ድል ይመራሃል።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር የእኛን እርሱን ማስታወስ አይፈልግም። እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ምሥጋናችንን ነው።