እዉነተኛ ፍቅር የህይወት ኀይል ነዉ

እዉነተኛ ፍቅር የህይወት ኀይል ነዉ

የምንኖረዉና የምንቀሳቀሰዉ፣ ያለነዉም በእርሱ ነዉና፡፡ – ሐዋ. ሥራ 17:28

ቅር የህይወት ኀይል ነዉ፡፡ ሰዎች በየጠዋቱ እንዲነቁና መሄዳቸውን እንዲቀጥሉ የሚያነሳሳቸዉ እሱ ነዉ፡፡ ፍቅር ለህይወት ዓላማና ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

ሰዎች ብዙ ጊዜ በህይወታቸዉ እንዳልተወደዱ ወይም ሊወዱት የሚችሉት ሰዉ እንደሌለ የሚያስቡባቸዉ ጊዜያት አሉ፡፡ ይህንን እይታ የሚያሳድጉት መልካም የሚመስሏቸዉን ነገሮች ለሟሟላት በመጀመሪያ አስበዉ ይጀምሩና ሲያጡ በፍርሃትና ተስፋ በመቁረጥ ዉስጣቸዉን ባዶ ያገኛሉ፡፡

ይሄ አጋጥሞት ያዉቃል? ፍቅርን ፈልጋችሁ ሄዳችሁ በመጨረሻም ያለመሟላት ስሜት ተሰምቷችሁ ያውቃል? አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ምን ዓይነት ፍቅር ነበር ስትከተሉ የነበረዉ?

አንተ ፍቅር እየፈለግህ ይመስልህ ይሆናል ነገር ግን እየፈለግህ የነበረዉ እግዚአብሔርን ነዉ ምክንያቱም እርሱ ፍቅር ነዉና፡፡ ያገኘሀዉ ማንኛዉም ፍቅር ከእግዚአብሔር ያልተገናኘ ከሆነ እርሱ ትክክለኛ ፍቅር አይደለም፤ ያለመሟላት ስሜት ጥሎብህ ነዉ የሚሄደዉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ “የምንኖረዉና የምንቀሳቀሰዉ፣ ያለነዉም በእርሱ ነዉና፡፡” ይላል፡ ይህ የሚነግረኝ ከእርሱ ዉጪ ህይወት ሙሉ እንዳልሆነች ነዉ፡፡

ሁሉም ፍቅርን ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ እየፈለክ ያለሀዉ የእግዚአብሔርን ፍቅር ነዉ? የሚየስፈልግህ፣ ዘላቂ የሆነና የሚያሟላህ ብቸኛዉ ፍቅር እሱ ነዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ከአንተ ያልሆነዉን ፍቅር በመፈለግ ያልተሟላ ህይወት መግፋት አልፈልግም፡፡ ከአንተ የማይገኝ ከሆነ እሱ እዉነተኛ ፍቅር አይደለም ምክንያቱም አንተ ፍቅር ነህና፡፡ ዛሬ ፍቅሬን በአንተ አግኝቻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon