እዉነትን መጋፈጥ ደስተኛ ህይወት ያመጣል

እዉነትን መጋፈጥ ደስተኛ ህይወት ያመጣል

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? – 2 ቆሮ 13፡5

ማንም ሰዉ ችግር እንዳለበት እስካላመነ ድረስ ከችግሩ ነጻ መዉጣት አይችልም፡፡ የአስካሪ መጠጥ፣ የዕጽ ተጠቂ ወይም ማንም ህይወቱን መቆጣጠር ያቃተው ሰው “እኔ ችግር አለብኝ እርዳታ እፈልጋለሁ” ለማለት እስካልበቃ ድረስ እዚያዉ ይሰነብታል፡፡

ከፈቃዳችን ዉጪ ችግሮቻችን መከራን ወደ ህይወታችን ቢያመጡም እንኳ ችግራችን አብሮን እንዲቆይና በዉስጣችን እንዲያድግ መፍቀድ የለብንም፡፡ ያለፈዉ ልምምዳችን ዛሬ ያለንብት አስቀምጦን ይሆናል ግን እዚሁ መቆየት የለብንም፡፡ አዉንታዊ እርምጃዎችን በመዉሰድ ነገሮችን ለመለወጥ መነሳሳት ይኑርህ ፤ ይህንን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ማድረግ እንችላለን፡፡

ምንም አይነት ችግር ቢኖሩብህ ፤ እዉነቱን ተጋፈጥ ሀላፊነትም ዉሰድ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችን እራሳችንን እንድንመረምር ያዘናል፡፡ ይኼ  ተስፋ አስቆራጭ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ኢየሱስ ስለማንኛዉም ያለፈ ችግርህና ሁኔታህ ሊረዳህ ይችላል፡፡

እዉነቱን ተጋፈጥ፤ የደስተኛ ህይወት ጅማሬ ሊሆን ይችላል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! በክህደትና ችግሬን በመፍራት  መኖር አልፈልግም፡፡ ራሴን ልመረምር መርጬአለሁ እናም አንተ ልትረዳኝ እንደምትችል በማወቅና ደስተኛ ህይወት ለመኖር  ወደ ችግሩ ስር ሄጄ እፈታለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon