እውነተኛ (ተግባቢ) አማኝ ሁን

እውነተኛ (ተግባቢ) አማኝ ሁን

‹‹… አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።›› (ኤፌ.2፡13)

አንድ ወቅት ‹‹ኃይማኖታዊ አማኝ›› ብዬ የምጠራው ነበር፤ በዚያን ጊዜ አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞኝ፣ በተወዛገበ፣ ተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኜ ሳለሁ በራሴ ምንም ዓይነት መፍትሔ ማምጣት ባልቻልኩበት እግዚአብሔርን ለእርዳታ ብቻ ጠየቅሁት፡፡ በተጨማሪ በዚያን ጊዜ ጸለይኩኝ፣ ብዙ አይደለም፣ ነገር ግን ጸለይኩኝ ምክንያቱም ያ ዓይነት ጸሎት ‹‹የኃይማኖታዊ (የሥርዓት) ጸሎት›› ዓይነት ነበር ያደረግሁት፡፡

‹‹ እውነተኛ አማኝ›› ብዬ የምጠራውን ዓይነት አማኝ ከሆንኩ በኋላ፣ ወዲያው መንፈስ ቅዱስ አጽናኜ፣ አስተማሪዬ፣ ወዳጄ፣ ረዳቴ መሆኑኑ ተማርኩኝ፡፡ ከዚም ያገኘሁት እውነት በሁሉም ነገር የእርሱ እርዳታ እንደሚያስፈልገኝ ማለትም ጸጉሬን ትክክል ለመሠራት፣ በውድድር ጥሩ ውጤት ለማምጣትና ለጓደኛዬ ትክክለኛ ስጦታ ለመምረጥ፣ እንዲሁም ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታዎች ውስጥ በምገባበትና አስቸጋሪ ፈተናዎች ሲገጥሙኝ በምወሰናቸው ትክክለኛ ውሳኔዎች ሁሉ የእርሱ እርዳታ እንደሚያስፈልገኝ ተረዳሁ፡፡

ኢያሱስ የሞተልኝ የተለየ አዲስ ዓይነት ኃይማኖት ሊፈጥርልኝ ፈልጎ ሳይሆን ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ጠበቀ ጥልቅ ህብረት ሊያመጣኝ እንደሆነ ይህ እውነት በትክክል ሲገባኝና በህይወቴ እርግጠኛ ስሆን ከ‹‹ኃይማኖታዊ አማኝነት›› ወደ ‹‹እውነተኛ አማኝነት›› ሽግግር አደረግሁኝ፡፡ እምነቴም እኔ እንደማስበው በማደርጋቸው መልካም ስራዎች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ነገር ግን በኢየሱስ ሥራዎች ላይ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ለእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ህብረት አድርጌ በእያንዳንዱ የህይወቴ ክፍሎች ላይ የእርሱን እርዳታ ለመቀበል፣ ድምጹንም ለመስማትና ከእርሱ ጋር ባለኝ የጠበቀ ወዳጅነት ደስተኛ ለመሆን እንድችል በር እንደከፈተልኘ አየሁ፡፡


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እውነተኛ አማኝ ሁን እንጂ ኃይማተኛ አትሁን

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon