ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ አሁንም ሆኖአል አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፣ ዮሐ. 4 23
ዓለም አብዛኛውን ጊዜ አምልኮን እንደ ‹‹ኃይማኖት›› ያስባልን ይሄ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሣብ ጋር የተቃረነ ነው፡፡ ሰዎች ሲጠይቁ የት ነው የምታመልከው;›› ይላሉ፡፡ እነርሱ በቀላሉ የት ቤተክርስቲያን እንደምንሄድ ለማወቅ ነው የሚፈልጉት፡፡ ስለ አምልኮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ የምናነበው ስለ ግል ግንኙነት ወይም ሕብረት እኛ ለእርሱ የምንናገርበት እና እሱ ለእኛ የምናገርበት ግንኙነት ነው፡፡ እምናነበው ስለመንፈሳዊ የጠበቀ ኅብርትና እግዚአብሔርን የሚወዱ ሰዎች በጥሞና እና በተመስጦ ውስጥ ሆነው ከልባቸው እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ነው፡፡ ይህ ነው እውነተኛ አምልኮ፡- ለእግዚአብሔር ያለን ፍላጎትና ጉጉት ሲኖረን ከውስጣችን ወደ ውጭ የሚፍለቀለቅ ከልብ የሆነ የሕይወት መሠጠት ነው፡፡
በዛሬው ጥቅስ መሠረት እግዚአብሔር እውነትን ይፈልጋል፡፡ እውነተኛ አምላኪዎችን ከእውነተኛ ልብ በእርግጥ ከመነጨ ፍቅር የሚያመልኩትን ይፈልጋል፡፡
ሁልጊዜ የሚያሳዝነኝ ነገር እግዚአብሔር የምፈልገው እውነተኛ አምላኪዎችን የሚፈልጉ እውነታ ነው፡፡ የሚገርመው የእኛ ቁጥር በጣም ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ የተረዳሁት እርሱ የሚፈልገው ማንም ሰው እንዲያመልከው ሳይሆን እውነተኛና ከልብ የሚያመልኩትን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ እርሱ የሚፈልገው በፍርሃትና እንደ ትዕዛዝ የሚያመልኩትን ሳይሆን ነገር ግን ከፍቅር በሆነ ግንኙነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፡፡
እውነተኛ አምልኮ ቤተክርስቲያንን ከመከታተልና ዝማሬን ከመዘመር በጣም ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ከውስጥ ከሕይወታችን ማንነት ማምለክ አለብን፡፡ ሁሉንም የምናደርገው ነገር ለእርሱና በእርሱ በኩል በማድረግ ነው፡፡ አምልኮ አምልኮ የሚመነጨው ከጠበቀ ሕብረትና ግንኙነት የሚመጣ እስከሆነ ድረስ ለእግዚአብሔር ድምፅ ያለብንን ስሜት ያነቃቃል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከፍርሃት የተነሣ አታምልክ ከፍቅር የተነሣ እርሱን አምልከው፡፡