እውነተኛ ደስታ

እውነተኛ ደስታ

በጉልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነው’ ያለውን የጌታን የኢየሱስን ቃል እናስታውስ፡፡ – ሐዋ 20፡35

ከአመታት በፊት ለሌሎች ስለመስጠት እግዚአብሔር ምን ያህል ግድ እንደሚለው አላውቅም ነበር፡፡ከዛ በፊት በራስ ወዳድነት የተሞላ፣ እራሴን አንደኛ ያደረገ ህይወት ነበር የምኖረው፡፡ለራሴ ደስታን ለማግኘት እታገልና እጥር ነበር፣ነገር ግን ሁልጊዜም እራሴን የማገኘው አቅቶኝ፣ተጨናንቄ እና ሳልደሰት ነበር፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ ሁለት ነገር ስለ እውነተኛ ደስታ አስተማረኝ፡፡አንዴ ደስታ ማለት ለሌሎች ሰዎች መልካምን ነገር በማድረግ ውስጥ የሚገኝ ውጤት መሆኑ ከገባኝ በኋላ በየቀኑ ሰዎችን ለመርዳት አውቄ መንገድን የመፈለግ ህይወትን እራሴን ማለማመድ ጀመርኩ፡፡

በሐዋሪያት ስራ 20፡35 ላይ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር “በጉልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነው’ ያለውን የጌታን የኢየሱስን ቃል እናስታውስ፡፡” ይላል፡፡

ይሄ ይገርማል፡፡መስጠት ከመቀበል በላይ ደስታን ይሰጣል? ከላይ ሲታይ ትርጉም አይሰጥም፡፡መቀበል በተጠናወተው አለም እና ባህል ውስጥ ነው የምንኖረው፡፡ብዙ ጊዜ ብዙ ነገሮች ያሏቸውን ሰዎች እናይና በእውነት ደስተኛ ሳይሆኑ አይቀሩም ብለን እናስባለን፡፡

ነገር ግን እውነተኛ ደስታ የሚመጣው ለሌሎች ሰዎች ከመስጠት የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡ይሄ ማለት ሚሊዮኖችን መስጠት አለባችሁ ማለት አይደለም፡፡እግዚአብሔር የሚጠይቃችሁ ያላችሁን እንድትሰጡ ነው፡፡

“ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት እረክቻለሁ” የሚልን ሰው በፍጹም መሆን አልፈልግም፡፡ በገሀዱ አለም ይሄ እርካታን የሚያመጣ ነገር አይደለም፡፡ምችለውን ያህል ሰው መርዳት እፈልጋለሁ፡፡

ዛሬ ልትሰጡት የምትችሉትን ሰው ፈልጉ፡፡ስጦታችሁ ምንም ያህል ትልቅም ሆነ ትንሽ ፣ገንዘብም ሆነ፣ጊዜ ወይም አበረታች ቃል ያላችሁን ስጡ፡፡በመስጠት ውስጥ ያለውን እውነተኛ ደስታ ተለማመዱ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ እውነተኛ ደስታ የሚመጣው ከመስጠት እንጂ ከመቀበል እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ከራስ ወዳድነት የመነጩ መሻቶቼን ረስቼ በዙሪያዬ ላሉት መስጠትን በመፈለግ የእውነተኛ ደስታን ህይወት መኖር እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon