ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 5:3
አእምሯችንን ማደስ አስፈላጊ ነው ፤ ሆኖም ግን ይህ የማደስ እና የመለወጥ ስራ ቀስ በቀስ የሚሆን እንደሆነ ማስተዋሉም አስፈላጊ ነው። ሂደቱ ቀርፋፋ ቢሆን ወይም በሂደቱ ውስጥ መጥፎ ቀን ቢያጋጥምህ ተስፋ አትቁረጥ። ቆም በል ፣ ትከሻህን አስተካክል ከዛም እንደገና ጀምር።
አንድ ህፃን ልጅ መራመድ ሲማር ቆሞ መሄድ እስኪችል ድረስ ብዙ ግዜ ይወድቃል ፤ ነገር ግን ልጁ ያለማቋረጥ ደጋግሞ ይሞክራል። ሲወድቅ ለተወሰነ ግዜ ሊያለቅስ ይችላል ነገር ግን እንደገና ቆሞ ይሞክራል።
አስተሳሰባችንን መቀየር መማር በተመሳሳይ መልኩ ይሰራል። ልንታገልና ልንወድቅ እንችላለን እግዚአብሄር ግን እኛን ለማንሳት ሁል ግዜ ከጎናችን አለ። ከመናደድ ይልቅ መከራችሁን ድል አድርጉ የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል በማስታወስ አከናውን። ምክኒያቱም ትግል ውስጥ መሆንህ በራሱ መልካሙን የእምነት ትግል እየተዋጋህ ነው ማለት ነው።
አሉታዊ አስተሳሰብ የሚኖረንና ሁሉን ነገር በትክክለኛው መንገድ የማናደርግበት ግዜ ሊኖር ይችላል ነገር ግን መቼም መሞከር ማቆም የለብንም። እኛ ተስፋ እስካልቆረጥን ድረስ እግዚአብሄር ቀስ በቀስ ወደርሱ አስተሳሰብ ያመጣናል።
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሄር ሆይ ፣ በምወድቅ ሰአት ስለምታነሳኝ አመሰግናለሁ። በመከራ ውስጥ ባለሁ ሰአት አሉታዊ አስተሳሰቦቼን እንድተው እና ይበልጥ ወደ አንተ አስተሳሰብ እንድመጣ በእኔ ውስጥ እንደምትሰራ አምናለሁ።