እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተሰምቶህ ያዉቃል?

እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተሰምቶህ ያዉቃል?

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፡፡ – ፊል 2፡3

ፊልጵስዩስ 2፡3 የሚለዉ ከራስህ ይልቅ ሌሎችን አክብር ነዉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሌሎችን የማስቀደምና አስፈልጎቶቻቸዉን የመሙላት ፍላጎት በዉስጣችን ማሳደግ ይፈልጋል፡፡ ሆኖም እንደዚህ ዓይነት ኑሮ መኖር አንዳንዴ አድካሚ ነዉ፡፡ እውነቱን ከተናገርን ሁላችንም ከራሳችን መንገድ ወጥተን ሌሎችን ለመርዳት የማንፈቅድበት ቀናት በህይወታችን አሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ለመርዳት ያሰብኳቸዉ መንገዶች ያደክሙኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቤተሰቤ ሁሉ ይፈልገኛል፣ ስራዬ ይፈልገኛል፣ ጓደኞቼ ይፈልጉኛል ሁሉም በተለያየ መንገድ ይፈልጉኛል፡፡

እጅግ እንደተፈለግሁ አስቤ አዉቃለሁ? አዎ! አንተም ቢገጥምህ ምንም ማለት አይደል፡፡ ሁላችንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ድካም ይሰማናል፡፡ ነገር ግን እርሱ እንድናደርግ የሚፈልገዉን ማንኛዉም ነገር እንድናደርግ እግዚአብሔር ጸጋን እንደሚሰጠን መረዳት አለብን፡፡

የሌሎችን አስፈልጎት ለማሟላት ድካም ሲሰማህ ወደ ፊል 2፡3 ሂድና መንፈስ ቅዱስን እርዳታ ጠይቅ፡፡ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ትሁት አድርግ እርሱ በህይወትህ አንተን የሚፈልጉ ሰዎችን እንድትረዳ ያበረታሃል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ከራሴ ይልቅ ሌሎችን ማስቀደም እፈልጋለሁ፤ ሌሎችን ለማገዝ ፍላጎት አጥቼ ስታገልና ድካም ሲሰማኝ አንተ እንድረዳቸዉ የምትፈልገዉን ሰዎች እንድረዳ ጸጋና ፍቅር ስጠኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon