“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል፡፡ መዝ፡ 19÷1
እግዚአብሔር ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ እርሱ ለሁሉም የሰው ልጅ ራሱን ገልፆዋል፡፡ ሮሜ 1፡19-20 እርሱ በፈጠራቸው ፍጥረትና በእጁ ሥራዎች ኃይሉና ዕቅዱ ግልፅ ሆኖ ይታያል፡፡
በማስተዋል ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔ ወደ ፈጠራቸው በዙሪያ ወዳሉት ፍጥረት ተመልከት፡፡ በእነዚህ ፍጥረቶች በኩል በእርግጥ እግዚአብሔር እንዳለ ትረዳለህ፡፡ እርሱ እለት እለት ወደ እኛ የሚያቀርበውና ማስረጃ በየቦታው ስለእራሱ በመተው ነው፡፡ እነዚህ ማስረጃዎች ደግሞ የሚሉት እኔ እዚህ ነኝ ያለሁት እኔ ስላለሁ አትጨነቅ፣ አትፍራ ነው የሚሉት፡፡
ፀሐይ በየማለዳው ወጥቶ በየማታው ይጠልቃል፡፡ ኮከቦች በየምሽቱ ወጥቶ በሰማይ ላይ ያደምቃሉ፣ የልማት ደግሞ በየሥርዓታቸው መቀጠላቸው የሚያመለክቱት የእግዚአብሔርን ጥበቃና አብሮነት ከእኛ ጋር እንደሆነ ማረጋገጫ ናቸው፡፡
በበጋ ወራት አንዳንድ ዛፎች ሙሉ በሙሉ የደረቁ ሲመስሉ፣ በክረምት ወራት ደግሞ ተመልሰው እነዚያው ሲያለመልሙ ስንመለከት፣ ልክ እንደዛው እግዚአብሔር ተስፋ የሌለውን ሕይወታችን መልሶ ያለመልማል፣ ምንም እንኳ ከሁኔታችን የተነሣ ተስፋና የሕይወት ትርጉም ቢጠፋብንም ሕይወታችንን እንደገና ያለመልማል፡፡
በሕይወቴ ነፍሳት ዛፎችን ወዲህና ወዲያ ሲያወዛውዝ ማየት በጣም ያስደስተኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ድንገት ንፋስ ይመጣና ደርቀው ለጊዜው በዛፉ ላይ የተንጠለጠሉትን የደረቁ ቅጠሎች በማራገፍ ሌላው ከሥር እንዲያቆጠቁጥ አጋጣሚ ይፈጥራሉ፡፡ ይህ የሚያስረዳኝ ታማኙ የእግዚአብሔር መንፈስ ንፋስ የሚያስፈልገውን ነገር ከሕይወታችን በማስወገድ ለአስፈላጊ የሕይወታችን ጉዳይ ቀጣይነት ይሰጣል፡፡ እነሱ በሕይወታችን አዲስና ልዩ ዕድገት እንዲሁም የተሃድሶ ዘመን ያመጣ፡፡ አስታውስ ይህ ምሣሌ የሚያሳየን እግዚአብሔር በተፈጥሮ እንዴት እንደሚነግረንና የእነሱን አስረጅነት ከሁሉ ነገር ማየት እንደሚቻል ነው፡፡
የዛሬ የእግዚብሔር ቃል በአንተ፡- ከብዙ አስረጅዎች አንዱን እይ እግዚአብሔር ዛሬ ለአንተ የተወልህን ማስረጃ ተመልከት