
«…አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል» (መዝ. 86፡ 11)።
የእግዚአብሔር ድምጽ የምንሰማውና ከሆነ እርሱን ለማገልገል ከፈቀድን ከእርሱ ጋር የምንታገለው ብዙ የትግል ጊዜያት እናስወግዳለን። ጥበብ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚፈልገው ሥራ እንዲሠራ እንፈቅድና ሁልጊዜ አንድን «ተራራ» መዞርንና ዙሪያ ጥምጥም መሄድን እንድናቆም ትነግረናለች (ዘዳ.2፡3)። እኔ እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር ያለበቸውና ለሃያና ሰላሳ ዓመታት ጊዜአቸው የባከነውን ሰዎች አግኝቼ አውቃለሁ። እነርሱ በቀላሉ ለእግዚአብሔር ታዝዘው ቢሆን ኖሮ የትና የት ብዙ ርቀት መጓዝ በቻሉ ነበር።
እግዚአብሔር በፈለገን ጊዜ ባለንበት ሥፍራ የቆየንበት ረጅም ጊዜ ቢሆንም ምንም ችግር የለውም። እርሱ ግን አሁን ባለንበት ሥፍራ እንድንቆይና የማንቀሳቀስ እንድንሆን አይፈቅድም። እርሱ ወደ አዲስ ሥፍራ ሊወስደን ወይም ወደ አዲስ ሥፍራ ሊስገባን፣ አዲስ ትምህርት ሊያስተምረን ዛሬም አለው።
እርሱ በህይወት ሙላት ውስጥ ሊያኖረን ይፈልጋል። ሊያሳድግንና በእርሱ ዕቅድና ዓላማ ሙላት ውስጥ ሊያኖረን ይፈልጋል። እግዚአብሔር እንዲህ ብሎናል «… በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥ እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥ ምክሬን ሁሉ ግን ቸል ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልፈቀዳችሁ፤ እኔም ስለዚህ በጥፋታችሁ እስቃለሁ፤ ጥፋታችሁም በመጣ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ፤ ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ ጥፋታችሁም እንደ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ፥ ጭንቅና መከራ በወረደባችሁ ጊዜ። የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም» (ምሳ. 1፡24 28)። እግዚአብሔር መሐሪና ታጋሽ ነው። ነገር ግን ይህን እኛ ለእርሱ ታዛዦች በሆንን ጊዜ በህይወታችን የምናረጋግጥበት ጊዜ ይመጣል። እኛ ፈጥነን ከታዘዝንና የእግዚአብሔርን መንገድ መኖር ከጀመርን በህይወታችን ፈጥነን በእግዚአብሔር ዕቅድ ወደ ፊት መራመድና ከእርሱ የምናገኘውን ማግኘት እንችላለን።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ጸልይ፣ ታዘዝ እናም አትዘግይ