እግዚአብሔርን ምሰሉ

እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች (አባታቸውን እንደሚመስሉ) እግዚአብሔርን ምሰሉ (ቅጂውን ሁኑና ምሳሌውን ተከተሉ)፡፡ – ኤፌ 5፡1

ክርስቲያን መሆን ማለት በየሳምንቱ ቤተ-ክርስቲያን መሄድ ማለት አይደለም፡፡ኢየሱስ ተግባራዊ በሆነ መንገድ ሲሰራ ሌሎች እንዲያዩት የእግዚአብሔርን ባህሪ ማዳበር አለብን፡፡

ኤፌ 5፡1 ሲናገር እግዚአብሄርን ምሰሉ ይላል፡፡ ያለመታደል ሆኖ ይህንን ቃል ከመኖር ይልቅ መናገር ይቀላል፡፡

ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን ጭራሽ የማያሳዩ ነገሮችን እናደርጋለን፡፡ ሲያቅተን ማዘን፣ተስፋ መቁረጥ እና እራሳችን ላይ መፍረድ ቀላል ነው፡፡

ተመስገን የሚያስብለው ነገር ገና መሆናችን እግዚአብሔርን የማይገደው መሆኑ ነው፡፡ሰው ብቻ መሆናችንን ያውቃል፡፡በአንድ ለሊት እርሱን መስለን እንደማናድር ያውቃል ነገር ግን በማደግ እንድንቀጥል ይፈልጋል፡፡

እምነታችን እየጨመረ ሳይሄድ በአንድ ቦታ የረጋ ህይወትን መኖር የለብንም፡፡ ይሄ ምኑ ደስ ይላል? ህይወታችንን ዞር ብለን ስናየው የተካሄዱ ለውጦችን ማየት መቻል አለብን፡፡

ፈሪሳዊ ነበርኩ፡፡የፈሪሳዊያን አለቃ መሆን እችል ነበር፡፡ሀይማኖተኝነት ላይ ጎበዝ ነበርኩ ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔርን “ለመምሰል” ምንም አላደርግም ነበር፡፡በአንድ ወቅት እግዚአብሔር ራሴን፡የበለጠ እግዚአብሔርን ለመምሰል ምን እያደረግኩ ነው? እየረዳሁት ያለ ሰው አለ ወይ? እዚህ ነገር ውስጥ ያለሁት እግዚአብሔር ህይወቴን እንዲያሻሽለው ነው?ብዬ እንድጠይቅ ረዳኝ፡፡

መጠየቅ ስንጀምር በጣም ጥሩ እያደረግን ነው፡፡ክርስቶስን የበለጠ ለመምሰል ሁልግዜ በመጣር ላይ ነን ማለት ነው፡፡

ስትጥሩ ከፍጱምነት እና ራስን ከመክሰስ ወጥመድ ተጠበቁ፡፡እኛ ሁላችን ስህተትን እንሰራለን ነገር ግን አስፈላጊው ነገር በየዕለቱ እግዚአብሔርን የበለጠ ወደመምሰል እርምጃዎችን ለመራመድ ፈቃደኛ መሆን ነው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ምንም እንኳ ስህተቶቼን ብታይም አሁንም ስለምትወደኝ እና እግዚአብሔራዊ ህይወትን እንድኖር ስለምትረዳኝ አመሰግናለሁ፡፡በውድቀቶቼ ተስፋ ላለመቁረጥና በተመሳሳይ መንገድ መቀጠልን ተቃውሜ አንተን መከተልንና በየዕለቱ አንተን የበለጠ መምሰልን እመርጣለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon