ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። – ሉቃ 6:38
አንዳንዶች ገንዘብን ወይም የዚህን ዓለም የንግድ ስርዓት ከእግዚአብሔር በፊት ያስቀምጡታል፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳችን በራዕይ 18 ላይ እምነታችንን በገንዘብ ላይ ካስቀመጥን እንደምንከስር ይናገራል፡፡ የገንዘብ ጉዳይ ቀላል እንደሆነ ደርሼበታለሁ፤ ከእግዚአብሔር በላይ ለመስጠት ሞክር (እዉነታዉ ከእግዚአብሔር በላይ መስጠት አትችልም ግን ስትሞክር ዉጤቱ አስደናቂ ይሆናል፡፡)
የበለጠ ስንሰጥ የበለጠ እንታዘዛለን የበለጠም ይባርከናል፡፡ ለሌሎች ሰዎች የበለጠ ባካፈልን ቁጥር ራሳችን የበለጠ ደስተኞች ሆን እና ነገሮቻችን ከቀደሞዉ በላይ ተሟልቶልን እናገኛለን፡፡
መህበረሰባችን በዓለም ስርዓት ላይ ኢንቬስት እንድናደርግና ሁሉንም ጊዜያችንን ገንዘብ ለመስራት እንድንጠቀም ይመክረናል፡፡ ይህንን ብናደርግ የሚጠቅመን ምንም አይኖረንም በተለይም ደስታ፡፡ ገንዘባችንንም ለመደሰት አንጠቀምበትም ምክንያቱም በእግዚአብሔር መንገድ አልተጠቀምንበትምና፡፡
በዓለም እይታ ምንም ስሜት ላይሰጠን ይችላል ነገር ግን እግዚአብሔር ገንዘብ ብቻ እንድትሰራና እንድታከማች አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔር የሚልህ አዉጥተህ በመስጠት በመጨረሻ ብዙ ይኖርሃል ይልሃል፡፡ ዛሬ ለጋሽነት እንድትጨምር እነግርሃለው፤ እመነኝ ከእግዚአብሔር የበለጠ መስጠት አትችልም፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ለፋይናንሴ ያለህ እቅድ እንደ ዓለም እንዳይደለ አዉቃለሁ፡፡ ነገር ግን አንተ ባልከዉ መንገድ መስጠት ስጀምር ስለ እኔ እንደምትጠነቀቅ አዉቃለሁ፡፡ ገንዘቤ የአንተ ነዉ እኔም አንተ እንደምትፈልገዉ እጠቀመዋለሁ፡፡