በአክብሮት እንዲፈራህና በትጋት እንዲያመልክህ ለባሪያህ የገባኸዉን ቃል ኪዳን አጽና፡፡ (መዝሙር 119:38)
እግዚአበሔር በቃሉ ይናገረናል፣ ቃሉም የመጣዉ ሊረዳን፣ ሊመራን በየዕለት-ተዕለት ኑሯችን ሊያበረታን ነዉ፡፡ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ሆነን ድምጹን መስማት እንችላለን ምክንያቱም በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ መጸለይ የሚያስችለን የቃሉን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ እናገኛለን፡፡ አንዳንድ ጊዜየእግዚአብሔር ቃል የሚያስደንቅ፣ ግልጽና ጥልቅ የሆነን ምሪት ይሰጠናል፡፡ሌላጊዜ ደግሞ ጥበብ የተሞላበትን ወይም መንፈሳዊ መርሆዎችን በነገሮቻችን ላይ መተግበር ይገባናል፡፡ ለምሳሌ፣ ቀጥለዉ የተዘረዘሩት ፣ ጠላታችን ሊዋጋን የሚችልባቸዉ በተለያዩ ስሜቶች ዉስጥ ስንሆን ለመጸለይ የሚረዱን የተለመዱ የቃሉ ክፍሎች ናቸዉ፡፡
- በከባድና አስቸጋሪ ሁኔታና ድካም ዉስጥ ስትሆን፣ ኢሳያስ 40፡ 29 አንብብ፡- “ለደካማኃይልንይሰጣል፥ጕልበትለሌለውምብርታትንይጨምራል።”
- የወደፊት ሆኔታ ሲያሳስብህ በኤርምያስ 31፡17 ላይ ያለዉን “ለፍጻሜሽምተስፋአለ፥” የሚለዉን ቃል መጸለይ ትችላለህ፡፡
- በኢኮኖሚና ኑሮ የምትቸገር ከሆነ በመዝሙር 34:9–10 ላይ ያለዉን “የሚፈሩትአንዳችንአያጡምናቅዱሳኑሁሉ፥እግዚአብሔርንፍሩት። ባለጠጎችደኸዩ፥ተራቡም፥እግዚአብሔርንየሚፈልጉትንግንከመልካምነገርሁሉአይጐድሉም።” የሚለዉን ቃል መጸለይ ትችላለህ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ጥያቄዎቻችን ሁሉ መልስ እንዳለዉና የሚያስፈልገንን ጥበብ ሁሉ እንደሚሰጠን አምናለሁ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ስሜቶቻችን ወደተሳሳተ መንገድ ይወስዱናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ደህንነት ይመራናል፡፡