እግዚአብሔርን በብዙም በጥቂቱም ታመን

አንተን ታምኛለውና በማለዳ ምህረትን አሳማኝ፣ አቤቱ ነፍሴን ወደ አንተ አንስቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ፡፡ መዝ 143 8

ለትላልቅ ክንዋኔዎችና ውሳኔዎች እግዚአብሔርን ለመስማትና ለመታመን የተማርኩባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ በትናንሽ ነገሮች እግዚአብሔርን በመስማት ነው፡፡

አንድ ጊዜ እኔና ባለቤቴ ዴቭ ከተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ጋር ተንቀሳቃሽ ፊልም ለማየት ፈልገን ነገር ግን ‹ሪሞት› ማግኘት አልቻልንም፡፡ ያለ ሪሞት ደግሞ ፊልሙን ማጫወት አንችልም፡፡ ስለዚህ ሁሉም በትጋት ብፈልግም ነገር ግን ፈልገን ማግኘት አልቻልንም፡፡ እኔ ለመፀለይ ወሰንኩ በዝግታ በልቤ እንዲህ አልኩ ‹‹መንፈስ ቅዱስ እባክህ ‹ሪሞቱ› የት እንዳለ አሳየኝ፡፡ ‹‹ወዲያውኑ በሃሣብ የመታጠቢያ ክፍል ስመጣ ሪሞቱን ከመታጠቢያው ክፍያ ስንፈል እዛ አገኝ ነው፡፡

እንዲህ የመኪና ቁልፌ ተመሣሣይ ነገር ገጠመኝና ብዙ ቦታ ካፈለኩት በኋላ እንዲያው ድካም ሆነብኝ ከዚያ ፀለይኩ ከዚያ በመንፈሴ ቁልፉን በመጀመሪያ የመኪና ወንበር ላይ አየሁ በእርግጥም እዛው አገኘሁት እነዚህ ሁለት ገጠመኞች የእውቀት ቃል የፀጋ ሥጦታ ምሣሌዎች ናቸው፡፡ (1 ቆሮ 12 8) እግዚአብሔር ስለ ሪሞቱና ስለመኪናው ቁልፍ አስመልክቶ የእውቀት ቃል ሰጠኝ፡፡ ይህ የዕውቀት ቃልና ሌሎች የፀጋ ሥጦታዎች በማንኛውም መንፈስ ቅዱስን በተሞላ ሰው ሁሉ ውስጥ አለ፡፡ እነዚህ መለኮታዊ የኃይል ሥጦታዎች ለአማኞች ከተፈጥሮ አካሄድ በላይ ለመኖር የሚያስችል መንገድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ይወደናል ስለሚጠነቀቅልን ይናገራል፡፡ ለምሣለ ለእኔ ጉዳይ ‹‹የእርሱ ንግግር›› ስለመኪና ቁልፍና ስለ ‹ሪሞት› ሃሣብና የሥላዊ መገለጥ ስሰጠኝ የሚያሳየው እግዚአብሔር ለጥቃቅን ነገሮች እንኳ ብሆን ለሕይወታችን እንደሚጠነቀቅ ያሳየናል፡፡ እግዚአብሔር ለትላልቅ ጉዳዮቻችንም ልናገረንና ሊመራን በጣም ጉጉት እንዳለሁ በእርግጠኝት ማሰብ ትችላለህ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ለአንተ በጣም ስለሚጠነቀቅልህ ስለጥቃቅን የሕይወትህ ጉዳዮች እንኳ ሊነገርህ እንደሚፈልግ አስታውስ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon