ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውሃ ምንጭ ትተውኛልና የተቀደዱትንም ጉድጓዶች ውሃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል፡፡ ኤር 2÷13
የመጀመሪያና ትልቁ የእያንዳንዱ ሰው ስህተት እግዚአብሔርን መተው ወይም ችላ ማለት ነው ወይም እርሱ እንደሌለ ዓይነት መንቀሳቀስ ነው፡፡ ኤርሚያስ የፃፈላቸው ሰዎች ይህንን ይመስሉ ነበር፡፡ በኋላ ላይ በዚሁ ምዕራፍ ሌላ ጥቅስ ‹‹ሕዝቤ ግን የማይቆጠር ወራት ረስቶኛል፡፡ እግዚአብሔር ስል እናያለን፡፡ (ኤር 2÷32 ተመልከት) እንዴት የሚያስፈራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማዘኑን ምናልባትም የብቸኝነትን ስቃውን ድምፁን ያስተጋባል፡፡
ልጆቼ ስለ እኔ ጉዳይ ማሰብ ብረሳ ደስ እንደማይለኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለብዙ ቀናት ከአንዳቸው ጋር ሳልነጋገር መቆየት አልችልም፡፡ ለአገልግሎት ወደተለያዩ ቦታዎች የምንቀሳቀስ ወንድ ልጅ አለኝ፡፡ ከባሕር ማዶ በሚሆንበት ጊዜ እንኳ ጥቂት ቀናት መሃል ይደውልልኛል፡፡
እኔና ባለቤቴ (ዴቭ) ከአንዱ ልጃችን ቤት ለሁለት ቀን እራት አብረን የበላንበትን ቀን አስታውሳለው፡፡ በሚቀጥለውም ቀን ዝም ብሎ ደውሎና እንደው ምን እያደረግን እንዳለንና አብረን የሆነ ነገር ብናደርግና በሚቀጥለው ምሽት አብረን እራት እንድንበላ ጋብዘን፡፡ እንዲሁም እኛ እነርሱን ለመርዳት የምናደርገውን ጥረት ለማመስገን ነው የደወለው፡፡
እንደዚህ ዓይነት ጥሩ ሕብረትን ለመገንባትና ለማጠንከር የሚረዱ ነገሮች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጥቂትና ትንሽ የምንለው ዋናውና ትልቁ ይሆናሉ፡፡ የልጆቼ ድርጊት እንደሚወዱኝ እርግጠኛ ያደርገናል፡፡ ደሞም ፍቅራቸውም እንዲሰማልኝ እርግጠኛ ያደርገኛል፡፡
በዚያው መንገድ ነው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚሆነው የተወደዱ ልጆች ምናልባት እንደምንወደው ያውቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ፍቅራችን በተግባር መለማመድ ደግሞ ይፈልጋል፡፡ በተለይ እርሱን ማስታወሳችንና ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ መፈለጋችንን ይፈልጋል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር ለአንተ ጉዳይ በሆነ ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ያደርግልሃል፡፡ ስለዚህ በነፃነት ሆነህ የሚሰማህን ማንኛውንም ነገር ንገረው፡፡