እግዚአብሔርን እመን መልካምንም አድርግ

እግዚአብሔርን እመን መልካምንም አድርግ

በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። – መዝ 37፡3

ብዙዎቻችን ለራሳችን እንዴት በረከት ማግኘት እንደምንችል ለማወቅ ስንጥር ብዙ ጊዜ አጥፍተናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ጠቃሚ ነዉ ብለዉ ያሰቡትን ለማጠናቀቅ ዘመናቸዉን ሙሉ ይጨርሳሉ፤ እግዚአብሔርን አያምኑትም እንዲመራቸዉም አይፈቅዱለትም፡፡ በመጨረሻም ይህ ለ ድብርትና አለመርካት አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡

መዝሙር 37፡3 የሚለዉ በእግዚአብሔር ታመን መልካምንም አድርግ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ራስ ወዳድና ዘወትር ራሳችንን ብቻ ለመርዳት የምናተኩር እንድንሆን አልፈጠረንም፡፡ ሌሎችን ለመርዳት መልካም ዘር እንድንዘራ ይፈልጋል፡፡ መልካምን ማድረግ ትልቅ እርካታ ያመጣልናል ምክንያቱም ለውጥን ማምጣት ያስደስታልና፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር እንዲባርክህ መንገድም ይከፍታል፡፡

እግዚአብሔር በህይወትህ ትክክለኛዉን በረከት እንደሚያመጣ እመን ፤ የእርሱን ትክክለኛ ጊዜ ስትጠብቅ ሌሎችን ለመርዳት ሰአትህን ተጠቀምበት፡፡ እርግጥ ሁሌ ስለ ራስህ የማታስብ ከሆነ ታጋሽ ትሆናለህ፡፡

ማድረግ እንዳለብህ የምታዉቀዉን መልካም ነገር እያደረግህ ስትባትል እግዚአብሔር በታማኝነቱ ይባርክሃል አስፈልጎቶችህንም ያሟላል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ራስ ተኮር የሆነ የስግብግብነት ኑሮ መኖር አልፈልግም፡፡ አንተ እንድወዳቸዉ የመራሀኝን ሰዎች በመርዳት ስባትልና መልካምን ሳደርግ ትክክለኛዉን በረከት በትክክለኛዉ ሰዓት ወደ ህይወቴ እንደምታመጣዉ አምነሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon