እግዚአብሔርን የተቀባይነታችሁ ምንጭ አድርጉት

እግዚአብሔርን የተቀባይነታችሁ ምንጭ አድርጉት

የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ – መዝ 46፡11

በዛሬ ዘመን ያለመረጋጋት እና የጭንቀት ወረርሽኝ ከህብረተሰባችን ውስጥ የህይወትን ደስታ እየሰረቀ በግንኙነቶች መሀል ብዙ ችግሮችን እየፈጠረ ነው፡፡ ያለመረጋጋት እና የጭንቀት ስሜት በሰው ህይወት ላይ የሚያመጣውን ውጤት ስላሳለፍኩት አውቀዋለሁ፡፡አንድን ሰው ምን እንደሚያደርገው አውቃለሁ፡፡

የደህንነት ስሜት የማይሰማቸው ሰዎች የሚሰማቸውን የበታችነት እና ተቀባይነት የማጣት ስሜት ለማሸነፍ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ያለማቋረጥ ይፈልጋሉ፡፡ የተቀባይነት ማግኘት ሱሰኞች ናቸው፡፡

ከያለመረጋጋት እና የጭንቀት ስሜት ጋር ስንታገል፣አንድ ነገር ብቻ ነው ነጻ የሚያወጣን እርሱም የእግዚአብሔር እውነት ነው፡፡እውነታው እግዚአብሔር በነጻ ፡ፍቅር፣ተቀባይነት፣ደህንነት፣ዋጋ ያለው ሰውነት እና ስፍራ ሰጥቶናል።

እርሱ መሸሸጊያችን ነው፣ማማችን፣ምሽጋችንም፣በአስቸጋሪ ወቅት መደበቂያችንም ነው (መዝ.9፡9፣31፣4፣32፡7፣37፡39፣46፡1ን ይመልከቱ) ። ዋጋችን፣ስፍራችን፣ተቀባይነታችን ሁሉ የሚመጣው ከእርሱ ዘንድ ነው። እነዚህ ነገሮች እስካሉን ድረስ በአለም ላይ እጅግ ውዱ ነገሮች አለን፡፡

ወደ እርሱ ስትመለከቱ፣ልትሆኑ የተፈጠራችሁትን በራሱ የሚተማመን፣የበሰለ ሰው በመሆን ወደ አዲስ የነጻነት ደረጃ ከፍ ትላላችሁ ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ለደህንነቴ ስሜት ወደ አንተ እመለከታለሁ፡፡መሸሸጊያ እና ብርታቴ የመሆንህ እውነትነት ላይ አተኩራለሁ፡፡ፍቅርንና ተቀባይነትን ሰጥተኸኛል፡፡በአንተ ብቻ ሙሉ ለሙሉ ደህንነት እንደሚሰማኝ እተማመናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon