እግዚአብሔር ለትሁታን ጸጋን ይሰጣል

እግዚአብሔር ለትሁታን ጸጋን ይሰጣል

ጎልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትህትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል”፡፡ – 1 ጴጥ 5፡5

አንደኛ ጴጥሮስ 5፡5 የሚነግረን እግዚአብሔር ትዕቢተኛዉን እንደሚቃዎምና ለትሁቱ ጸጋን እንደሚሰጥ ነዉ፡፡ እናም ማንም ራሱን እንደሰራ የሚቆጥር ወንድ ሆነ ሴት ክፉ ነገር ይመጣባቸዋል፤ ኢየሱስ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም እንዳለዉ ነዉ፡፡ (ዮሃንስ 15፡5)

በትዕቢት እየኖርን ፤ ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ስኬትን ለማግኘት መሞከር ማለት ለብዙ የጠላት ጥቃት የተጋለጥን ነን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ትሕትና የእግዚአብሔርን እርዳታ ወደ ህይወታችን የሚጠራ መሸፈኛ ነዉ፡፡ “እግዚአብሔር ሆይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላዉቅም አንተን እታመናለሁ” ብለህ ራስህን ትሁት ስታደርግ እግዚአብሔር ይረዳሃል፡፡

በእርሱ ካልተደገፍንና ካልታመንን እግዚአብሔር በአንዳች ነገር እንድንሳካ አይፈቅም፡፡ ነገር ግን ከሐይለኛዉ እግዚአብሔር እጅ ስር ራሳችንን ትሁት ስናደርግ በጊዜዉ ከፍ ከፍ ያደርገናል(1ጴጥ 5፡6ን ተመልከት)፡፡ በጊዜዉ ማለት የእግዚአብሔር ጊዜ ነዉ፤ እኛ እንደተዘጋጀን ስናስብ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደተዘጋጀን ሲያዉቅ፡፡ ይህንን በተረዳንበት ፍጥነት እግዚአብሔር በህይወታችን ያለዉን ዕቅድ ይሰራል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በጊዜዉ ከፍ እንደምታደርገኝ አዉቄ ራሴን በፊትህ አዋርዳለሁ፡፡ በራሴ መንገድ መሳካት ስለማልችል የአንተን እርዳታ እሻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon