እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ይናገራል

እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ይናገራል

እግዚአብሔርም አለ፡- እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለውን; ዘፍ፡ 18 17

ማንም ሰው እንደ አብርሃም ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ›› የሚባል ሰው ምናልባት ይኖራል ብዬ አላስብም፡

፡ ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ዳዊትን ‹‹እንደ ልቤ የሆነውን ሰው አገኘሁ›› ብልም ለዮሐንስ ደግሞ ‹‹ጌታ የምወደው ደቀመዝሙር›› ብባልም፣ አብርሃም ግን ለየት ያለ ክብር ያለውና የእግዚአብሔር ወዳጅ ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ተጠቀሰው ለዚህም ነው፡፡

እግዚአብሔር በሰዶምና በጎመራ ሕዝብ ክፉ ሥራ ላይ አምላካዊ የቁጣ ፍርድ ሊያፈስ በወሰነ ጊዜ ለአብርሃም ምን ለማድረግ እንዳሰበ እቅዱን ነገረው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አብርሃምን እንደቅርብ ወዳጁ ቆጥሮት ነበርና ነው፡፡ ልክ አንተ ለማድረግ ያቀድከውን ለጓደኛህ እንደምታጨውተው እግዚአብሔር ለአብርሃም ሊያደርግ ያለውን ነገረው፡፡ አብርሃምም በሰዶምና በጎሞራ ላይ ስለሚመጣው ጥፋት በሰማ ጊዜ ቀርቦ ‹‹በውኑ ፃድቁን ከኃጥያተኞች ጋር ታጠፋለህን; (ዘፍ 18 23 ተመልከት) እግዚአብሔር ለአብርሃም እቅዱን እንዳካፈለው አብርሃምም በግልጽና በድፍረት ቀርቦ ስለእቅዱ ተናገረ፡

፡ ምክንያቱም እነርሱ ለእርስ በርስ ወዳጆች ናቸውና፡፡ በነፃነት ሆኖ የሚገናኙበት የጠበቀ ኅብረት ነበራቸው፡፡ አብርሃም እግዚአብሔር ለአንተም ወዳጅ ለመሆን ይፈልጋል፡፡ ለአንተ ልንገርህና አንተም የምትለውን ለመስማት ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ሙሉ በሙሉ እንደ አዲስ ተቀብለህ እግዚአብሔር ለአንተ በእርግጥ የቅርብ ወዳጅህ አድርገህ እሱን በዚህ መልክ ዛሬ ተቀበል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረትን አጠንክር ከእርሱ ጋር በነፃነት ሆነህ አናግረው ደግሞ በቀላሉ እርሱ የሚነግርህን ስማው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon