እግዚአብሔር ሊባርከን ይፈልጋል

እግዚአብሔር ሊባርከን ይፈልጋል

«እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም» (መዝ.84፡11)።

በህሊናችን በኩል መንፈስ ቅዱስ አንድ የሠራነውን ስህተት አንድ እርሱ ያሳዘነው ነገር ከእርሱ ጋር ባለን ህብረት መካከል ጣልቃ የገባውን ነገር ወይም በህይወታችን የእርሱ ህልውና እንዳይሰማን ምክንያት የሚሆነውን እንድናውቀው ያደርጋል። በተጨማሪም እርሱ ወደ ምንፈልገው ወደ ትክክለኛው ቦታ እንድንመለስ ይረዳናል። እርሱ በኃጢአታችን ይወቅሰናል። እንዲሁም ያሳምነናል። ነገር ግን እርሱ ፈጽሞ አይኮንንም።

እኛ ልጆቻችንን ከምንወደው የበለጠ እርሱ እኛን ይወደናል። በዚህ ፍቅሩ እርሱ ይቀጣናል /ዲሲፕሊን ያደርገናል/ ልጆቼ ህጻናት በነበሩበት ጊዜ የተሰጣቸውን መልካም ዕድሎች ሁሉ እወስድባቸው የነበረውን እጅግ እንዴት እንደምጠላው አስታውሳለሁ። ነገር ግን እነርሱ እኔን መስማት ባይማሩ ኖሮ በምን ያህል ችግር ውስጥ እንደሚገቡና እንደሚታሠሩ አውቃለሁ። እግዚአብሔርም እንዲሁ ዓይነት ተመሳሳይ ትኩረት ለእኛ አለው። እርሱ ግን ታጋሽ ነው።

እርሱ ደግሞ ደጋግሞ ይናገረናል አሁንም ይናገረናል። ምን ማድረግ እንዳለብን ምናልባት እርሱ የእኛን ትኩረት ለማግኘት በመሞከር አሥራ አምስት ጊዜ በተለያዩ መንገዶች ተናግሮን ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ለራሳችን መልካምነት እንድንታዘዘው ስለሚፈልግ ነው።

የእግዚአብሔር የፍቅር ወቀሳ መልዕክት በሁሉም ሥፍራ አለ። እርሱ ስለሚወደን እርሱን እንድንሰማው ነው። እኛ በራሳችን መንገድ ላይ ጸንተን የምንቆም ከሆነ እርሱ ለእኛ ያዘጋጀውን በረከቶችና ዕድሎች ይይዝብናል። ነገር ግን እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት የእርሱ በረከት በእኛ ላይ ሊያፈስስ ወደሚችልበት የብስለት ደረጃ እንድንመጣ ስለሚፈልግ ነው። እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን በነጻ ከሰጠን እኛ የምንፈልጋቸውን በረከቶች ሊከለክለን ውም ሊይዝብን አይፈልግም። እርሱ ፍለጎታችንና የተትረፈረፈ በረከቶቻችን ጋር ሊያገናኘን እንደለ መቁጠር እንችላለን።

ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ምንም እንኳን ዲሲፕሊን በሚያደርግህ ጊዜ ውስጥ እንኳን ብትሆን እግዚአብሔር ሊባርክህ ይገፈልጋል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon